Saturday, February 22, 2014

ኦሮሞ የUN አባል አይደለም እንዴ? ወላይታስ?



ከሰሞኑ የፌስ ቡክ ጓደኛችን እንደርታ መስፍን <የሀገር ፍቅር> በሚል ርዕስ መጣጥፍ አቅርቦ ነበር፡፡ እኔም ፅሁፉን ስለወደድኩት ሼር አደረግሁት፡፡ ታዲያ የፌስቡክ አለምን ከተቀላቀለ 5 አመት 4 ወር ቢሆነውም እስካሁን <ለአቅመ ሼርንና ፖስትን ልየታ> ያልደረሰ አንድ ፀሃፊ /ግርማ ካሳ ይባላል/ ፀሃፊው እኔ መስዬው እንዲህ ሲል ትችቱን ጀመረ፡

ከበደ ካሳ የሚባሉ አፍቃሪ ኢሕአዴግ ግለሰብ “አንዳንድ ሰዎች «ብሄር?» ተብለው ሲጠየቁ «ኢትዮጵያዊ» እያሉ የሚመልሱት፣ የራሳቸዉን ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አድርገው ያስቀመጡና በራሳቸው ማንነት የሌሎቹን ለመጨፍለቅ የሚያልሙ – የቅዠት ታንኳ ቀዛፊዎች ናቸው…. ተዛብታችሁ ሌላንም ለማዛባት ለምትፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ብሄር አይደለም። ኢትዮጵያ ሃገር እንጂ የአንድ ሕብረተሰብ ክፍል መለያ አይደለም።” የሚል አባባል ፌስቡክ ላይ ለጥፈው አነበብኩ>>"

አቶ ግርማ በዚህ የእኔ ባልሆነ ፅሁፍ መነሻነት ልቤ እስኪጠፋ ቀጠቀጠኝ፡፡ እሱ የእኔ መስሎት የተቸውን ከእንደርታ መስፍን ሀተታ የተቀነጨበ አንቀፅ ሙሉ በሙሉ የምደግፈው በመሆኑ እኔም ለተሰነዘረብኝ ጥቃት ይህን ረጅም የመልሶ ማጥቃት ፅሁፍ አዘጋጀሁ፡፡ ልብ በሉ፤ የቅራኔያችን መነሻ የሆነው ነጥብ <ብሔር ሲጠየቁ ኢትዮጵያዊ እያሉ መመለስ የራስን ማንነት በሌሎች ላይ ለመጫን የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጅ ብሔር ስላልሆነ> ‘ማለቴ’ ነው፡፡

Wednesday, February 12, 2014

መስራታችሁን ካላቆማችሁ ማውራታችንን አናቆምም- ግብፅ




ትናንት ማለትም ጥር 04/2006 የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ባዘጋጀው አንድ አውደ ጥናት ላይ ተሳትፌ ነበር፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ምሁራን ተሳትፈዋል፡፡ የመነጋገሪያ አጀንዳችን ደግሞ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፡፡ በዚህ ዝግጅት ሁለት ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን ግድቡን በተመለከቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የውይይቱን ይዘት በመገናኛ ብዙሃን እንደተከታተላችሁትና ቀሪውን ደግሞ ሰሞኑን በሚወጡ ጋዜጦች እንደሚዘገብ ተስፋ በማድረግ የእኔን ቀልብ ወደሳበው አንድ ጉዳይ ልምጣ፡፡


እንደምታስታዉሱት ከዚህ እለት ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ የውሃ፤ መስኖና ኢነርጂ  ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑ እና የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ሞሃመድ አብዱል ሙታሊብ በአዲስ አበባ ውይይት አድርገው ነበር፡፡ ስለዚህ ውይይት ውጤት የኛው ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑ ማብራሪያ ሰጥተውናል፡፡ እርሳቸው እንዳሉት ውይይቱ ያለስምምነት ነው የተቋጨው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ግብፅ ከአሁን በፊት አቅርባቸው የነበሩና በኢትዮጵያና በሱዳን ተቀባይነት ያላገኙትን ሀሳቦች {መተማመን የመገንባት መርህና የግድቡን ተፅዕኖ የሚያጠና ሌላ አለም አቀፍ ኮሚቴ ማቋቋም} አሁንም ዳግም ይዛ በመምጣቷ ነው፡፡

Monday, February 3, 2014

መክሸፍ እንደ ጎንደሩ ሰልፍ

Gonder 1
Gonder 2
Gonder 3
እውነቴን ነው የምላችሁ፤ አትሳደቡ፡፡ ልክ ስትሳደቡ የምረዳው ነገር ቢኖር እውነት ከናንተ ጋር እንዳልሆነች ነው፡፡ አሁን ትናንትና ጎንደር ከተማ ውስጥ የተካሄደው የሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፍ ምን ያህል ሰው እንደወጣበት በፎቶ ወይም በቪዲዮ አሳዩኝ ስላልኩ ይህ ሁሉ ስድብ ሊወርድብኝ ይገባል አንዴ? ስድባችሁ ያስረዳኝ ስትፅፉ የነበረው የውሸት መሆኑን ነው፡፡ ለነገሩ አይደንቀኝም፤ ምክንያቱም እውነት ተናግራችሁ ስለማታውቁ፡፡
ቆይ ያን ሁሉ የፅሁፍ መልዕክት በፌስቡክ ስትለቁልን፤ /ህዝቡ እየጎረፈ ነው፤ ከተማዋ በሞንታርቦ ተደበላለቀች፤  አደባባዮች ተጨናነቁ…/ ምስል ያጠራችሁ ሰልፉ ፌስቡክ ላይ ካልሆነ /ወይም በኔ አገላለፅ ኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ካልሆነ/ በስተቀር እንዴት የተቀረፀ ነገር ይጠፋዋል?
እስኪ ሁለት ንፅፅሮችን ላሳያችሁ፡፡