Saturday, June 22, 2013

የአባይ ፖለቲካኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን የፍሰት አቅጣጫ በግዜያዊነት ማስቀየሯ በተፋሰሱ ሀገሮችና በቀጠናው የተለመደ ሙቀት ላይ የፖለቲካ ትኩሳት ጨምሮበታል፡፡
ኢትዮጵያ ገና የግድቡን መገንባት ጅማሮ ባበሰረችበት ወቅት የያዘችውን የጋራ ተጠቃሚነት መርህ በዚህ ወቅትም እየደጋገመች ስታነሳ ግብፅ ደግሞ “ምንም አዲስ የተፈጠረ ነገር የለም”፤ “ተራ የምህንድስና ስራ ነው” በሚል ትኩሳቱን ለማብረድ ሞክራለች፡፡ ያም ሆኖ የሶስትዮሽ አለም አቀፍ የአጥኝዎች ቡድኑ የጥናት ሪፖርቱን ለሶስቱም መንግስታት ማቅረቡን ተከትሎ በጭምብል ተሸፍኖ የነበረው የግብፅ አቋም እርቃኑን እየወጣ ነው፡፡
በብርሃን ፍጥነት የተቀየረው የግብፅ አቋምና የዲፕሎማሲ ውጤቶቹ፤ የናይል ተጠቃሚነት ሁኔታና ምቹ ሁኔታዎች የዚህ ፅሁፍ ትኩረቶች ናቸው፡፡
አባይ ለማን ነው?

Sunday, June 16, 2013

ለምን ጋሪውን ከፈረሱ እናስቀድማለን?አንዳንድ ሰዎች የኢቲቪን የኃላ ታሪክ በመዘከር የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲያስተላልፍ ያሉበትን ድክመቶች በማህበራዊ ድረ-ገፆች ሲተቹ ተመለከትኩ፡፡ ዛሬ ዋልያዎቹ ከባፋና ባፋና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ የደቡብ አፍሪካ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባለሙያዎች ሙሉ በሙሉ የስርጭቱ ባለቤት ሆነው ስለሰሩት እንዲህ ያማረ ጨዋታ በቴሌቪዥን መስኮት አየንም ተባለ፡፡ እውነታውን በኋላ እመለስበታለሁ፡፡
እኔ የምለው ግን ካሁን በፊት ራሱን እግር ኳሱንስ እንጫወተው ነበር እንዴ? አናውቅም እንዴ የእግር ኳስ ታሪካችንን? ርግጥ ነው ቀረፃውንና ስርጭቱን አንችልበትም፡፡ ግን ጨዋታውንም አንችልበትም ነበር እኮ፡፡ ታዲያ ከፈረሱ በፊት ለምን ጋሪውን እናስቀድማለን? አሁን እግር ኳሳችን እያደገ ነው፡፡ ኢቲቪም አቀራረቡን አብሮ ያሳድጋል ብለን ተስፋ ማድረግ አይሻልም ትላላችሁ?
የዛሬውን ቀረፃ ያካሄደው ደግሞ የሳውዝ አፍሪካ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አይደለም፡፡ የስርጭቱ ባለቤት ከሆነዉ ፊፋ ኮንትራቱን አሸንፎ ይህን ጨዋታ ያሰራጨዉ በዘርፉ እውቅና ያለዉ አውሮፓዊ ኩባንያ ስፖርት ፋይፍ ነው፡፡ ይህ ኩባንያ ቀረፃውን ያካሄደው በስምንት ካሜራ ነው፡፡ ኢቲቪ ስምንት ካሜራ እንኳን ለእግር ኳስ ለብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀንም መድቦ አያውቅም፡፡ ብዙዎቹን የአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታዎች በአንድ ካሜራ ነው የሚቀርፀው፡፡ ታዲያ ባለሙያው ከወዲያ ወዲህ ሲንከራተት ጎል የሆነች ኳስ ብታመልጠው እንኳን ይገርማል እንዴ?

Monday, June 10, 2013

We are dependable and predictable to our neighbors


I don’t know why it is; but I was expecting the worst to come. Good to hear President Moursi of Egypt concluding his speech at the national conference saying, "We need to have a good relation with the People of Ethiopia, We don't want to have enemy."
President Moursi was somehow friendly while beginning his speech. He speaks about the trilateral commissions and says Egypt’s relations are improving with the Nile basin countries especially Ethiopia. Moursi said Egypt is having talks with Sudan and Ethiopia and notifies Egypt do not want to harm to them.
However, his full speech was not as soft as it were at the beginning. He rather boosted Egyptians are “the soldiers of God, and are not afraid for conspiracies or threats from East or West.”

Saturday, June 8, 2013

“ይህ ባንዲራ የኛ እንዳልሆነ አታውቁምን?”

የሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፍ አሁንም አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል፡፡ በሰልፉ ወቅት የብዙዎችን ቀልብ ያልሳበው ነገር ግን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜናው ከታየ በኋላ ብዙዎችን በማህበራዊ ድረ-ገፅ እያነጋገረ ያለው የሰንደቅ አላማው ጉዳይ ነው፡፡
አሁን አሁን እንደማነበው ነገሩ እየተጋነነና እየተዛባ የሚነገርበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ራሱ ወያኔ ሰማያዊ ፓርቲን በህዝብ ለማስጠቆር በገንዘብ ሰዎችን ገዝቶ የፈፀመው ሴራ ነው ከሚሉት አንስተው ሰንደቅ አላማዋን በእግራቸው ሲረጋገጧት አይቻለሁ እስከሚሉት ፅንፎች ድረስ ማለቴ ነው፡፡
በእለቱ በተላለፈው የኢቲቪ ዜና ላይ ሰልፈኞች ሰንደቅ አላማዋን ሲያጎሳቁሏት ይታያሉ፡፡ መነሻው ምንድን ነው? ለምንድንስ አጎሳቆሏት? ባንዲራዋንስ ማን አመጣት? የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሳት ተገቢ ነው፡፡ በኔ እምነት እነዚህን ጥያቄዎች በትክክል ለመመለስ ከድርጊቱ ፈፃሚዎች ቀጥሎ ከኔ የሚቀርብ ሰው የለም፡፡

Tuesday, June 4, 2013

ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት Vs ሼክ ሻኪር

እየተገፋሁ፤ እየተሰደብኩ ስኳትን ለዋልኩለት ለሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍማ አንዲት ቁራጭ ዜና ብቻ ፅፌ አልቆምም፡፡ ከጠዋቱ 300 ሰዓት እስከ ቀትር 800 ሰዓት የነበረው ሂደት እኮ በሚገርሙ፤ በሚያዝናኑና በሚያበሳጩ ትዕይንቶች የተሞላ ነበር፡፡ እናም ላሁኑ አንዱን መዘዝኩ፡፡
ወደ ኋላ ሶስት ወር ልመልሳችሁ፡፡ በየካቲት ወር በዋሽንግተን ዲሲ የታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት’ እንዲፈቱ የሚጠይቅ አንድ መድረክ ተዘጋጀ፡፡ ግብፃዊ አሜሪካዊው ሼክ ሻኪር በዚህ መድረክ ተገኝተው እንዲህ አሉ፡፡
“መልካሙን ዜና ልንገራችሁ፡፡ በቃ አሸባሪ ብለው ፈርጀውናል፡፡ ቤታችሁ ብትቀመጡም፤ ቴሌቪዥን እያያችሁ ብትሆኑም፤ ቡና እየጠጣችሁ ብትሆኑም፤ ተኝታችሁ ብትሆኑም ወይም ደግሞ ከልጆቻችሁ ጋር እየተጫወታችሁ ብትሆኑ አሸባሪ ናችሁ፡፡ ምክንያቱም እናንተ ሙስሊም ናችሁና፡፡”
ተጨበጨበላቸው፡፡