Thursday, May 30, 2013

ስለ አባይ ምን ተባለ? /የተሻሻለ/


ኢትዮጵያ ከትናንት ግንቦት 20/2005 የአባይ ወንዝን የተፈጥሮ አቅጣጫ መቀየሯ የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ሀገራት መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡ ዋናው ጉዳይ ምሽት ላይ አልጀዚራ በኢንሳይድ ስቶሪ /inside story/ ፕሮግራሙ ከኢትዮጵያ አቶ በረከት ስምዖንን፤ ከግብፅ ላማ ኤል ሃሎንና ከእንግሊዝ ሊዮ ፓስካልን በማስገባት ዉይይት ያደረገበት ነው፡፡ በዚህ ላይ በኋላ እመለስበታለሁ፡፡ አሁን ግን መገናኛ ብዙሃን፤ ግብፅና ሱዳን ምን አሉ የሚለዉን እንመልከት፡፡

በጉዳዩ ላይ ሰፊ ዘገባ የሰጠው አህራም የተባለዉ የግብፅ ድረ-ገፅ ነው፡፡ ቢቢሲ፤ አልጀዚራና ዋሽንግተን ፖስትም እንዲሁ፡፡ ሁሉም ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን በተለያየ መጠን ለጉዳዩ ሽፋን ሰጥተውታል ማለት ይቻላል፡፡ ከብዛታቸውና ከምንጫቸው ተመሳሳይነት አንፃር የያንዳንዱን ዘገባ አቅጣጫ ከማየት ይልቅ በዚህ ጉዳይ ላይ በስፋት አስተያየታቸውን ወደሰጡት ግለሰቦች አትኩሬአለሁ፡፡
ከላይ ከቁንጮው እንነሳ፡፡ ማለቴ ከግብፅ መንግስት አቋም፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት /ቤት ያወጣው መግለጫ አሁን በአባይ ወንዝ ላይ እየተካሄደ ያለው ግንባታ በውሃ መጠኑ ላይ መቀነስን ያስከትል የሚችል እንዳልሆነ የሚገልፅ ነው፡፡ በአባይ ላይ የሚገነባ ማንኛውም ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት የወንዙን አቅጣጫ በማስቀየር ቦታውን ለግንባታ ምቹ ማድረግን ይጠይቃል ብሏል መግለጫው፡፡ ስለሆነም ከተለመደው ውጭ የሆነ አዲስ ነገር የለም የሚል ይመስላል፡፡

Thursday, May 23, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ


ባለፈው አመት በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወቅት የእስልምና እምነትን ሽፋን ያደረጉ ሃይሎች "ጉባዔው ሲካሄድ ከመላው አለም ለመጡ መሪዎችና ለመገናኛ ብዙሃን ድምፃችንን ለማሰማት ከየአካባቢው ተሰባስባችሁ አዲስ አበባ ላይ ክተቱ" በሚል ያስተላለፉት አዋጅ መንግስትን አስከፍቶ ነበር፡፡


ያኔ ነገሩ አላማረም፤ እንዳይሆን ሆኖ ሰልፉም ተበላሸ፡፡ የያኔዎቹ ታዲያ ከስህተታቸው የተማሩ ይመስላሉ፡፡ በየሳምንቱ አርብ በሶላት ወቅት የሚነገቡ መፈክሮችን እየቀረፀ በማኅበራዊ ድረ-ገፆች የሚያሰራጭ አንድ የፌስቡክ ገፅ "ነገ አዲስ አበባን ሳይጨምር በመላ አገሪቷ የሚካሄደውን የተቃውሞ መርሐግብር ለማሳካት የሚደረጉ ዝግጅቶች በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ" ሲል ዛሬ በግድግዳው ላይ ለጥፏል፡፡  

ይህ የሚያሳየው ለእንግዶቹ ክብር ሲባል ከአርብ ጀምሮ አዲስ አበባ ላይ ብቻ ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ሰልፍ ወይም ግርግር እንደማይኖር ነው፡፡ ይህ ድረ-ገፅ በስቅለት እለትም ለክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላም ስንል የዛሬውን ተቃውሞ አንስተናል የሚል ፅሁፍ እንዳስነበበን አስታውሳለሁ፡፡

Wednesday, May 22, 2013

What a surprise!


What a sruprise! President Isaias Afwerki is the Chancellor of the University of Asmara and the chairman for the department of Eritrean Studies.
The University of Asmara has been reopened to give courses by September 2013 as announced yesterday on the occasion of the 22nd anniversary of Eritrea’s independence.

Tuesday, May 14, 2013

የብሄር ጥያቄ

ትናንት ምሽት ከስራ ወደ ቤቴ እንደገባሁ ባለቤቴ “ልጅህ የጠየቀችኝን ልንገርህ?” አለች፡፡  እሺ ስል ለማዳመጥ ጆሮዬን ሰጠሁ፡፡ ባለቤቴ እንደነገረችኝ ለልጃችን ከሱቅ ብስኩት ትገዛላታለች፡፡ ከዛ በዋጋ ጉዳይ ከባለሱቁ ጋር ስትነጋገር ሚጣ ጣልቃ ትገባለች፡፡ ልብ በሉ ሚጣ ገና የአራት አመት ልጅ ነች፡፡
 
ሚጣ፤ በቃ አንድ ብር ጨምሪለት
እናት፤ እሺ የኔ ጉራጌ፤ ስለ ብርም አውቀሽልኛል
ሚጣ፤ እንዴ እናቴ፤ እኛ ጉራጌ ነን እንዴ?
እናት፤ አይደለንም
ሚጣ፤ ኦሮምኛ ነን?
እናት፤ አይደለንም
ሚጣ፤ ታዲያ ምንድን ነን?
እናት ኢትዮጵያዊ ነን
ሚጣ፤ እሺ ኢትዮጵያዊ ነን፤ ግን የምንጨፍረው ምንኛ ነው?
እናት፤ አላውቅልሽም እሱን የሚያውቀው አባትሽ ነው፡፡

ቤቴ አምሽቼ ስገባ ልጄ ተኝታለች፡፡ ጠዋት ስትነሳ ወይም አንድ ቀን ትዝ ሲላት ይህን ጥያቄ ማንሳቷ አይቀርም፡፡ 

ባለቤቴ በእናቷ አማራ፤ በአባቷ ደግሞ ኦሮሞ ነች፡፡ እኔ ደግሞ በአባቴም በእናቴም አማራ ነኝ፡፡ ልጄ ታዲያ ብሄሯ ምንድን ነው የሚሆነው? መቸም ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጅ ብሄር አይደለም፡፡