Monday, April 22, 2013

ራስን በመውደድ ላይ ሳይሆን ሌሎችን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ዘረኝነት

በዩኔስኮ በተመዘገበ በኢሉ አባቦራ ዞን በሚገኘዉ የያዩ ደን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መረጃ ለጠየቃችሁኝና መረጃ ለሌላችሁ በሙሉ
እኔ ባለኝ መረጃ መሰረት አሁን እሳቱ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ነገር ግን ላለፉት 15 ቀናት ያክል በተለያዩ አካባቢዎችና አቅጣጫዎች እሳቱ እየተነሳና በአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ መልሶ እየጠፋ ነዉ የቆየ፡፡ ተከታታይ የሆነ እሳት አልነበረም፡፡ ላለፉት ጥቂት ቀናት ግን እሳቱ በመስፋፋቱ የመከላከያ ሰራዊትና የአካባቢ ነዋሪዎች በጋራ ተረባርበዉ አጥፍተውታል፡፡ የእሳቱ መንስዔ እስካሁን ባለ መረጃ ማር የሚቆርጡ ግለሰቦች እሳቱን እንዳስነሱት ነዉ የሚያመለክተ፡፡ ሆኖም በአካባቢ ባልተለመደ ሁኔታ ያጋጠመ የዝናብ መጥፋት ችግሩን አባብሶት ነበር፡፡ አሁን ግን ዝናብም መጣል ጀምሯል፡፡ 

ማህበራዊ ድረ-ገፅን ለእንዲህ አይነት በጎ አላማ ማለትም መፍትሄ ለማፈላለጊያ መጠቀም ፎቶ ሲለጥፉና ሼር ሲያደርጉ ከማዋል በእጅጉ ተመራጭ ፡፡ ነገር ግን የመረጃ እጥረትን እንደ እድል በመጠቀም አንዱን ብሄር በሌላዉ ላይ ለማነሳሳት መሞከር ርካሽ ተግባር ነዉ፡፡ ከጤናማ አዕምሮ የሚመነጭም አይደለም፡፡

የያዩ ደን እንኳን የኦሮሚያ ብቻ የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት ብቻ የሆነበት ግዜም አልፏል፡፡ በዩኔስኮ የአለም ቅርስነት ስለተመዘገበ ማለቴ ነዉ፡፡ ያም ሆኖ የኦሮሚያ ደን መቃጠል የማያንገበግበ ኢትዮጵዊ ካለ እሱ ራሱን ይፈትሽ፡፡ በዚህ ደን መቃጠል ሌላው ብሄር ምኑም እንዳልተነካ ብሎም እጁ እንዳለበት የፃፋችሁ ግን ያዉ ለናንተ እንዳፈርን ከመኖር ውጭ ምን እናደርጋለን፡፡ ከዚህ የባሰ ራስን በመደድ ላይ ሳይሆን ሌሎችን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ዘረኝነትስ የት ይገኛል?

በነገራችን ላይ እሳቱ ያደረሰ ጉዳት በጫካው አለም አቀፍ እዉቅና ላይ ጥያቄ በሚያስነሳ ደረጃ አይደለም፡፡ ይህን ጠብቃችሁ የነበራችሁ አልተሳካላችሁም፡፡ ሀብታችንን ላተረፉ፤ የመርዶ ነጋሪዎችን አፍ ላሲያዙ ለኢሉ አባቦራ ነዋሪዎችና ለጀግና መከላከያ ሰራዊታችን ክብር ይገባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ደኑ አለም አቀፍ ሃብት ሆኖ እንዲመዘገብ ከፍተኛ ጥረት አድርጎ ተሳክቶለታል፡፡ ይህንን ጠብቆ የማቆየት ሃላፊነት እንዳለበት የሚዘነጋ አይመስለኝም፡፡ ለዛም ነው የክልሉን የደን ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተርን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎችም በስፍራ በመሄድ የማዳን ተግባሩን ያስተባበሩት፡፡

እያንዳንዱን ክስተት ለበጎ ስራ እንጅ ርካሽ አላማን ለማስፈፀሚያ አንጠቀምበት፡፡


Post a Comment