Monday, April 29, 2013

ምቾት የሚባል በሽታ

1993 ክረምት፤ ለማትሪክ ፈተና ዝግጅት የማደርግበት ወቅት፡፡ ያኔ እንደብርቅ ከምናያቸ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ስጥ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑቱ የእረፍት ግዜያቸ የመሃል ሜዳ ///ሚካኤል //ቤት ባዘጋጀ የማትሪክ ማዘጋጃ መርሃ ግብር እኛን ተስፈኞቹን ይደግፉን ነበር፡፡ 
በትምህርት ክፍለ ግዜ መሃል ታዲያ የሃይማኖት ትምህርትም በደብሩ ሰባኪ ይሰጠን ነበር፡፡ ፈረንጆቹ ነፃ ግብዣ የለም/no free lunch/ እንደሚሉት ማለት ፡፡ እናም ፅድቅ ለነፍሱ የሻተ ሆነ ቀትን ለስጋ የፈለገ ስብከቱን ይከታተላል፡፡ እኔ ሁለቱም ጣፍጦኝ ስለነበር በንቃት ነበር የምከታተለ፡፡
ሰባኪ ደግሞ በጣም አሳታፊ ነበር፡፡ እሱ የሚለ ብቻ ሳይሆን እኛም የተረዳንን እንድንነግረ ያበረታታናል፡፡ እሱ ጌታ ማርያምን ‹‹አንቺ ሴት ከሳሾችስ የታሉ?›› አላት ካለ በኋላ ምን አላት?” ብሎ ይጠይቀናል፡፡ እኛም ንቁዎቹ  ከሳሾችስ የታሉ? አላት ስንል እንመልሳለን፡፡ ይሄኔ ይችም እውቀት ሆና እጅግ አድርጎ ያደንቀናል፡፡ እኛ እግዜርን እየፈራን እንጅ ምን አላት?” ሲለንአላት ብንል እንኳን የሚያደንቀን ይመስለኛል፡፡
ይህ ሰባኪ ታዲያ አንድ ቀን ስለሰዶም ሰዎች ሃጢያት እየነገረን ሳለ የሰዶም ሰዎች መጠጥ ወደዱ፤ ዝሙት ወደዱ፤ ጭፈራ ወደዱ፤ በአጠቃላይ ምን ልበላችሁ…” ብሎ ወደኛ ሲያይ እኔ እጄን እንኳን ሳላወጣ ምቾት ወደዱ አልኩት፡፡ ምቾት የሚለ ቃል ሁሉንም የሃጢያት ምንጮች ስለጠቀለለለት ይመስለኛል ሰባኪ በጣም አደነቀኝ፡፡ ምቾት የሚባል በሽታ…” እያለ ስብከቱን ቀጠለ፡፡ ምቾት የሚባል በሽታ
ለዚህ ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ በጅግጅጋ ከተማ የተካሄደ የፋይናንስና ገቢዎች ዘርፍ ጉባዔ በተመለከተ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈ አንድ ዜና ነዉ፡፡ በዜና ላይ መድረኩን የሚመሩት ሶስት ሰዎች ምስል ተደጋግሞ ይታያል፡፡ በቀኝ በኩል ያለ የስራ ሃላፊ የተቀመጠበት ወንበር በተለይ በጣም ግዙፍና ዙሪያ በስፖንጅና በቆዳ የተለበጠ ፡፡ የጀርባና የጎን መደገፊያ በሙሉ ወፍራምና ምቾትን የሚያጎናፅፍ መሆኑን ያየ ሁሉ በቀላሉ ይረዳዋል፡፡ ምስሉን ሳይ ቀድሞ ወደ አዕምሮዬ የመጣዉ ታዲያ ለጅግጅጋ ይህን ያህል ወንበር ምን ያደርግላታል?” የሚል ጥያቄ ነዉ፡፡
የሶማሌ ክልል ልዩ ድጋፍ ከሚሹ ክልሎች አንዱ ፡፡ ጅግጅጋ ደግሞ የሶማሌ ክልል ዋና ከተማ፡፡ የሶማሌ ክልል ልክ እንደሌሎቹ ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች የመሰረተ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚነቱ ምንም እንኳን እየተሻሻለ ቢመጣም አሁንም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ፡፡ ለዚህም ነ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የበጀት ክፍፍል ቀመር መሰረት እነዚህ  ክልሎቹ ይበልጥ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር የተዘረጋ፡፡
ለጅግጅጋ ይህን ያህል ወንበር ስል ከተማዋን አሳንሼ ከማየት አይደለም፡፡ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ችግር ግዙፍና ምቹ ወንበሮች ወይስ የተማሪ አግዳሚ ወንበሮችና የትምህርት ቁሳቁሶች የሚል ሀሳብ ስለመጣብኝ እንጅ፡፡ ደግሞ በጅግጅጋ ሙቀት ለዛውም በስብሰባ አዳራሽ ስጥ የዚህ አይነት ወንበር ትርፉ እንቅልፍን መጋበዝ እንጅ ምን ሊሆን ይችላል? እንደኔ እንደኔ እዚህ አዲስ አበባም ቢሆን ከምቾት ቀድሞ መደፈን ያለባቸ ብዙ ቀዳዳዎች አሉን፡፡
ለነገሩ ሆድ ያባ ብቅል ያወጣዋል እንዲሉ ሆኖብኝ እንጅ እኔን ያስከፋኝ የጅግጅጋ ወንበር ወይም እሱ ላይ የተቀመጠዉ ሃላፊ አይደለም፡፡ ነገሩን ልብ ብሎ ለተመለከተ /የእኔ አመለካከት ካልተዛባ በስተቀር/ ይህ ምቾት የሚባል በሽታ በርካቶችን እየለከፈ ይመስለኛል፡፡ በቢሮ ቁሳቁስ፤ በመኪናና በሌሎች አላቂ እቃዎች አጠቃቀማቸዉ አግራሞትን የሚያጭሩ ሞልተዋል፡፡
በአንዳንድ ሃላፊዎች መኪና በት ተመስጠን አቦ እንዴት የሚያምር መኪና ነዉ እያልን አድናቆታችንን ገልፀን ሳንጨርስ ሌላ ብና ድንቅ መኪና ይቀይራሉ፡፡ ከዛም ከአፍታ በኋላ እንዲሁ ይቀጥላል፡፡ እነኛ መኪናዎችም እየተንጠባጠቡ /trickle down/ ወደ ትንንሾቹ ሃላፊዎች ይደርሳሉ፡፡
በአንዳንድ /ቤቶች ያሉ የሃላፊ ቢሮዎችም ምድር ላይ ያሉ ገነት ይመስላሉ፡፡ በቢሮ ዉስጥ የተለያዩ አይነት ማራኪ ወንበሮች፤ ሶፋዎች፤ ጠረንጴዛዎች፤ ጌጣጌጦች፤ ወዘተተከማችተ ይገኛሉ፡፡ በነገራችን ላይ በቢሯቸዉ ዉስጥ ከሚቀመጡበት ወንበር፤ ከጠረንጴዛ፤ ከእንግዳ ማረፊያና ከመፅሃፍ መደርደሪያ ውጭ ኮተት የማያበዙ ሃላፊዎችንም አልዘነጋኋቸዉም፡፡
ታዲያ ከሁሉም ሃላፊዎች ቢሮ /በተለይ ከቅርብ ግዜ ወዲህ/ የማይጠፋ አንድ ፎቶ አለ፡፡ ለነዚህ አይነት ቅንጡ ህይወት ያልተፈጠረ የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ፎቶ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዉርስ /legacy/ በክፉም በበጎም ብዙ አነጋግሯል፡፡ /በዚህ አጋጣሚ በዚሁ ጉዳይ በብሎጌ ላይ 'ማንን እንመን?‘whom to believe?’ በሚል ርዕስ ያሰፈርኩትን ፅሁፍ እንድታነቡት ደግሜ ጋብዣለሁ፡፡/ ጭፍን ጥላቻ ከተጠናወታቸው በስተቀር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማንም በቅንጡነት ሲያማቸዉ ግን አልሰማሁም፡፡ ይልቁንም ለግል ህይወታቸ ሳይጨነቁ ያለእረፍት መስራታቸዉ ሙሉ መግባባት /consensus/ ላይ የተደረሰበት ጉዳይ ነዉ፡፡ እነሆ የእኝሁ ታላቅ መሪ ፎቶ ግድግዳ ላይ ተሰቅሎ የአንዳንዶችን ቅንጡነት ይታዘባል፡፡
ልብ ብላችሁ ካያችሁ ይሄ ምቾት ያልኩት በሽታ በሃላፊዎች ብቻ ሳይወሰን ያለአቅማቸዉ በሚንጠራሩ ሌሎች ሰራተኞችና የግል ባለሀብቶችም ይስተዋላል፡፡ በአንዳንድ /ቤቶች ሚኒስትሩ እንኳን ያልተቀመጠበት ወንበር ላይ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዉ ተቀምጦበት እናያለን፡፡
እነዚህ ነገሮች ምንም አዎንታዊ አስተዋፆ የላቸዉም ብየ አልከራከርም፡፡ የእንግዶችን ምቾት መጠበቅ፤ በጎ ገፅታ መገንባት፤ ወዘተሊነሱ ይችላሉ፡፡ በዚያኛዉ ጎን ያለዉ አሉታዊ አስተዋፆ ስለሚያጋድል እንጅ፡፡
በርግጥ ለዚህ ለሚንደላቀቁበት ሃብት መገኘት እነዚህ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች የላቀ ሚና ተጫዉተዋል፡፡ ምክንያቱም አሁን ሀገራችን የደረሰችበት እድገትና እየዘመነ ያለዉ የኑሮ ደረጃችንም ቢሆን በነሱ ግንባር ቀደም መሪነት በሰፊዉ ህዝብ ተሳትፎ የመጣ ነዉና፡፡ ሆኖም ድርጊታቸዉ የተገኘችዉን ፍሬ ገና ሳትበስል የመሸምጠጥ አይነት በመሆኑ ሃይ ሊባሉ ይገባል፡፡ በየትኛዉም የሃላፊነት ደረጃ ቢሆን የእኔ ኑሮ የሚለወጠዉ የአጠቃላይ ህዝቡ የኑሮ ደረጃ ሲለወጥ ነዉ ብሎ ማሰብን ይጠይቃል፡፡
በልፋታችን ልክ እንውሰድ ከሆነማ የሀገሪቱን ሀብት የቀድሞዎቹ የኢሕአዴግ ታጋዮች የአሁኖቹ የሀገር መሪዎች ተከፋፍለዉ በጨረሱት ነበር፡፡ ኢሕአዴግ የድህነት ጠበቃ የነበረዉን የደርግ ስርዓት ለመጣል ባደረገዉ እልህ አስጨራሽ ትግል ዉስጥ ታጋዮቹ መራር መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ ከድል በኋላ ግን የይገባኛል ጥያቄ አላነሱም፡፡ ይልቁንም ታግለን የጣልነዉ የድህነትን ዘበኛ እንጅ ድህነትን አይደለም ብለዉ ለሌላ የፀረ-ድህነት ትግል ነዉ ራሳቸዉን ያዘጋጁት፡፡
እናንተዬ ትንሽ ነገሩን ከረር ሳላደርገዉ የቀረሁ አይመስለኝም፡፡ ቅናት ብጤም ሳይሰማኝ አልቀረም፡፡ በሉ ደህና ሁኑ፡፡
Post a Comment