Sunday, April 14, 2013

ተስፈኛዉ "መንግስት" የቦንድ ሽያጭን አወገዘ


በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በህመም ላይ ሳሉ ሃገራችን ገደል አፋፍ ላይ ቆማለችና እንታደጋት ብለዉ በአሜሪካ ምድር ኢትዮጵያን የሚገዛ አንድ ተስፈኛ መንግስት አቋቋሙ፡፡  ስመሙንም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር መንግስት ምክር ቤት አሉት፡፡  

ዛሬ ይህ የሽግግር ምክር ቤት ለዩናይትድ ስቴትስ ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ ኮሚሽን /SEC/ የፃፈዉ ደብዳቤ በአዉሮፓ ምድር ያሉ የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎችን አቋም ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነዉ፡፡ በአጭሩ የደብዳቤው ይዘት የህዳሴ ቦንድ የሚባል ነገር በአሜሪካ መሸጡ ይቁም፡፡ የገዙትም ገንዘባቸው ይመለስላቸዉ የሚል ነዉ፡፡

በውጭ ያሉት ተቃዋሚዎች በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የኢትዮጵያ ህዝብ ምርር ብሎ ሲያዝን ቢመለከቱት ጭንጋፍ የሕዝብ ርኩስ፤ የርጉም ዘመን ልጆች፤ የሬሳጀግና፤ ወዘተ… ሲሉ የስድብ መዓት አወረዱበት፡፡ የኛዉ አልበቃ ብሏቸዉ በፍርፋሪዋ የምታኖራቸውን ሀገር ከፍተኛ ዲፕሎማት ሱዛን ራይስን ዘለፉ፡፡ መለስን በተመለከተ በጎ የተናገሩትን ሁሉ ጥላሸት ለመቀባት ባለ በሌለ ሃይላቸዉ ተረባረቡ፡፡


ተቃዋሚዎቹ እያንዳንዷን ጥቃቅን ስህተት ወይም ስህተት ነች ብለው ያሰቧትን ጉዳይ ለራሳቸዉ ጥቅም ማስፈፀሚያ ለመጠቀም ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ በማንሸዋረር የፖለቲካ አጀንዳቸዉን ለማሳካት ተራሯሩጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሙስሊሞችን በገዛ ሀገራቸዉ ሁለተኛ ዜጋ አድርጓቸዋል ሲሉ የአዞ እንባ ተራጭተዋል፡፡

ይሄ ሁሉ ድካማቸዉ ጉም የመዝገን ያክል ቢሆንባቸዉም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የጀመሩትን ዘመቻም ጎን ለጎን ቀጥለዉበታል፡፡ ወደ ዘመቻዉ ሲገቡ በአባይ ጉዳይስ ማንም አይሰማንም ከሚል ስጋት በመነጨ ፍራቻ እጅና እግራቸዉን እየጎተቱ ነበር፡፡ አሁን ግን የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንዲሉ እስከ ጥፍራቸዉ ተነክረዉበታል፡፡

ግድቡ የሚሰራዉ አንድ ግዜ የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገሪቱ በተከሰተዉ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ዉድነት ላይ የሚያነሳዉን ጥያቄ ለማፈን ነዉ ሌላ ግዜ ደግሞ የአረቡ አለም ህዝባዊ አብዮት ወደዚህ እንዳይመጣ ሃሳብ ለማስቀየር ነዉ አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ኑሮዬ ቢከፋም ለግዜያዊ ችግሬ ዘላቂ መፍትሄ ይሆነኛል ላለዉ የህዳሴዉ ግድብ ከሌለዉ ላይ ቀንሶ መስጠቱን ተያያዘዉ፡፡

ቀጠል አደረጉና ሃገሪቱ በሌላት አቅም እንዲህ አይነት ግዙፍ ፕሮጀክት ከምትገነባ እዚህና እዚያ ትናንሽ ግድቦችን ብትገነባ ነዉ የሚያዋጣት ሲሉ ምሁራዊ መሰል የአዛኝ ቅቤ አንጓች አስተያየታቸዉን ሰጡ፡፡ ለዚህም ጆሮ ያዋሳቸዉ የለም፡፡ ብዙ ተባለ ብዙ ሰሚ ግን አልተገኘም፡፡ 

የግድቡ ግንባታ እዉን እየሆነ ሲመጣ ደግሞ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ለህዳሴዉ ግድብ የቦንድ ሽያጭና ድጋፍ ማሰባሰብ በሚደረግባቸዉ አዳራሾች በመዞር ገንዘብ እንዳይዋጣ ለማድረግና ከቻሉም ዉይይቱን ለመበተን በመባከን ወገባቸዉን አጎበጡ፡፡ በሳዉዲ አረቢያ፤ በደቡብ አፍሪካና በቅርቡም በአሜሪካ የተካሄዱ መድረኮችን በአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡ በተቃራኒዉ የኢሳትን ትኬት ግዙ፤ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ማተሚያ ማሽን መግዣ ገንዘብ አዋጡ እያሉ የአላፊ አግዳሚውን ህሊና ያቆስላሉ፡፡

እኒህ የሃገራቸዉ ስኬት አይናቸዉን የሚያቀላቸዉ ሃይሎች ዘመን ያለፈበት የአዉሬ ፊልም በማህበራዊ ድረ-ገፆች በማሰራጨት ግድቡ በፈጣሪም የተጠላ ነዉ በማለት ለመስበክም ዳድቷቸዋል፡፡ የግድቡ ባለቤት እኔው ነኝ እያለ በሚመካዉ ህዝብ ስሜት ላይ ቀዝቃዛ ዉሃ ለመቸለስ በግድቡ የኢትዮጵያ ድርሻ 49% ብቻ ነዉ፤ ቀሪው የአንዲት አዉሮፓዊት ሃገር መሆኑን ደርስንበታል ሲሉ ዘፍነዉም ነበር /ምንም እንኳን ከሁለት ቀናት የዘለለ እድሜ ባይኖረውም/፡፡ ይሄ ሁሉ እንግዲህ ከተለመደዉ ለኢትዮጵያ ብድርና እርዳታ መስጠት ይቁም ዉትወታቸዉ ውጭ ያለዉ ነዉ፡፡

እነዚህ የተቃዋሚ ሃይሎች በየግዜዉ አስመራ እየተመላለሱ መመሪያ መቀበላቸዉ ሳያንሳቸው ሰሞኑን ደግሞ በግብፅ ካይሮ ቢሮ ለመክፈት ማቀዳቸዉ ተሰምቷል፡፡ በዚህና በቀደመው ተግባራቸዉ የኢትዮጵያ ጠላት የመሰላቸዉ ሁሉ ወዳጃቸዉ፤ የኢትዮጵያን ወዳጅ ሁሉ ጠላታቸዉ አድርገዉ ማመናቸዉን በተግባር አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ግን በነዚህ ሁሉ የአብራኩ ክፋይ የሆኑ ሟርተኞች የገጠመዉን ፈተና ተቋቁሞ በራሱ አቅም የግድቡን ግንባታ ቀጥሏል፡፡ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለግድቡ የሚውል ቦንድ እየተሸጠ ነዉ፡፡ 

አሁን ታዲያ የበሠበሠ ዝናብ አይፈራም እንደሚሉ አንዴ ገብተንበታል በሚል በአሜሪካ እየተካሄደ ያለዉ የቦንድ ሽያጭ ህገወጥ ነውና አስቁምልን ሲሉ የአሜሪካንን መንግስት ተማፅነዋል፡፡ በነገራችን ላይ ‘የኢትዮጵያ ህዳሴ’ የሚለው ሃረግ ስለሚያንገበግባቸው በትክክለኛ አጠራሩ ‘የህዳሴዉ ግድብ ቦንድ’ በማለት ፈንታ “የአባይ ወንዝ ግድብ ቦንድ” በማለት ነው በማመልከቻቸዉ የጠቀሱት፡፡

ኢትዮጵያዉያን ገንዘብ አዋጥተዉ ግድብ ሊሰሩ ነውና የአሜሪካንን መንግስት እጃቸዉን ይያዝልን ሲሉ ግልፅ ደብዳቤ ለዩናይትድ ስቴትስ ሴኪሪቲስ ኤክስቼንጅ ኮሚሽን /SEC/ ፅፈዋል፡፡ ከአሌክሳንደሪያ ቨርጂንያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት ቢሮ በዚህ ሳምንት አጋማሽ ለኮሚሽኑ የተላከዉ ደብዳቤ “ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ በኢትዮጵያ መንግስት እየተካሄደ ባለዉ የቦንድ ሽያጭ ላይ ምርመራ እንዲካሄድበት እዚህ አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስም እንጠይቃለን” ይላል፡፡

እንግዲህ ይሄን የሚለዉ ከመለስ ሞት በኋላ የ4ኪሎውን ቤተ-መንግስት ለመረከብ አስቦ በአሜሪካ ቴክሳስ የተቋቋመዉ ምክር ቤት ነዉ፡፡

ደብዳቤዉ የቦንድ ሽያጭ እየተካሄደ ያለዉ ለዚህ ተግባር ስልጣን በሌለዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካኝነት ነዉ፤ የተሰበሰበዉ ገንዘብም የት እንደሚገባ አይታወቀም የሚሉ መነሻዎቸን ያስቀምጣል፡፡

በመሆኑም የዩናይትድ ስቴትስ ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ ባለሃብቶችን የመጠበቅ፤ ፍትሃና ዉጤታማ የገንዘብ ዝዉዉርን የማረጋገጥ ግዴታ ስላለበት በጉዳዩ ላይ አፋጣኝ ምርመራ በማድረግ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጠን እንጠይቃለን” ይላል ማመልከቻው፡፡ ነገሩ ዶሮ ሰምታ ታንቃ ሞተች እንደሚሉት መሆኑ ነዉ፡፡

የሽግግር መንግስቱ በደብዳቤዉ መጨረሻ ፍላጎቱን በ8 ነጥቦች አጠቃሎ አስቀምጧል፡፡ እነዚህም፤
1.      በአባይ ወንዝ ቦንድ ላይ መግለጫ ይሰጠን፡፡
2.     የአሜሪካ መንግስት ቦንዱ እዚህ እንዲሸጥ ፈቃድ ሰጥቶ ከሆነ ማብራሪያ ይስጠን፡፡
3.     በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይህን አይነት የቦንድ ሽያጭን ለማመቻቸት ህጋዊ ስልጣን አለዉ ወይ?
4.     ይህ ትክክል ካልሆን SEC በኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ምን አይነት ማጣራትና እርምጃ ይወሰዳል? ለህዝብ ይፋ ቢሆን፡፡
5.   በቦንዱ ሽያጭ ህጋዊነት ላይ የሚመክር ህዝባዊ መድረክ ስላመቻቸን SEC በመድረኩ ለመሳተፍና አቋሙን ለማንፀባረቅ ፈቃደኝነቱን ቢገልፅልን፡፡
6.     የቦንዱ ሽያጭ ህገወጥነት ከተረጋገጠ ሽያጩ በአፋጣኝ እንዲቆም የሚወሰደዉ ርምጃ ምን ይሆናል?
7.     ቦንድ በመሸጥና በማመቻቸት በተሳተፉ ሰዎች ላይ የሚጣልባቸዉ ቅጣት ቢነገረን፡፡
8.     እስካሁን ቦንድ የገዙ አሁን ግን እንዲመለስላቸዉ የሚፈልጉ ካሉ SEC የሚያደርግላቸዉ ድጋፍ ምን ይሆናል?

“የሽግግር መንግስቱ አመራሮች በፈረንጆቹ ሚያዚያ 27/2013 በቺካጎ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ እንደታሰበ ሰምተናል፤ ስለሆነም ምላሹ ከዛ ወዲህ ይሰጠን” ሲሉ የጅብ ችኩልነታቸውን በደብዳቤያቸው አረጋግጠዉልናል፡፡
 
በማጣራት ሂደቱ ሁሉ ከአሜሪካ መንግስት ጎን አንቆማለን ያሉት እነዚሁ ‘መሪዎቻችን’ በደብዳቤው ያላካተቱት ቢኖር ለሚደረግልን ትብብር አስቀድመን እናመሰግናለን የሚለዉን አረፍተ ነገር ብቻ ነዉ፡፡ የማይነበብ ፊርማ አለ፡፡ ከሰላምታ ጋርም አለ፡፡
የምክር ቤቱን ሙሉ መግለጫ ሊንክ ወይም ከዚህ በታች word format ያገኙታል፡፡

Ethiopian National Transitional Council

 United States Securities Exchange Commission (SEC)
85 S. Bragg Street, Suite 203
Alexandria, VA 22312, USA Tel: 1-202-735-4262

Subject: Public inquiry into the legality of sale of “Nile River Investment Bond by the
Ethiopian Government here in the United States.

We are writing on behalf of Ethiopian-Americans and other Ethiopians residing here in the United States, who have been asking us to inquire on their behalf about the legality of the sale of bonds for the construction of Nile River Dam in Ethiopia by the Ethiopian Government here in the United States that has been taking place for the last few years. Most of the inquirers complain that the government did not give them adequate information on the way their investments are spent, their legal rights and in fact on the legality of the sale itself. Although the Ethiopian Government has been engaged in the bond sale process for a number of years, so far, those who invested in the bonds complain that they have no clue as to where the money went. On the contrary, information coming out of the country indicates that the money is being used to illegally enrich certain companies and individuals affiliated with the Government and it is wasted unnecessarily. There is virtually no accountability and transparency on the way their investments are handled. Consequently, many are extremely disappointed and feel that they are were cheated out of their investments

This so calledNile River Dam Bond sale scheme here in the United States is masterminded, planned, organized and led by the Embassy of Ethiopia in Washington, DC and is spearheaded by the Ambassador, Girma Birru. Many wondered if the Embassy and Ambassador have the mandate to get involved in this kind of project. Hence, as there is total confusion, despair, disappointment, misinformation and sense of betrayal, we can no longer continue to give a blind eye to the situation. Hence since the Ethiopian National Transitional Council (ENTC) is an institution established to advocate for the rights of Ethiopians all over the world, we felt that we have the right to demand from the Securities Exchange Commission (SEC) a serious inquiry and public explanation on this very urgent issue which is, the sale of Nile River Bond in the USA by the Ethiopian Government through its embassy here in the United States We believe that the Securities and Exchange Commission (SEC) is charged with protecting investors and maintaining fair and efficient capital markets. SEC regulations govern the activities of individuals and organizations involved in the sale of securities, including brokers and brokerage firms. Hence, we feel that the SEC has the legal responsibility to provide comprehensive explanation on the questions we list below.


1.     The legality of the sale ofNile River Bond” sale here in the USA.
2.     Clarification on if and how the Government secured license to advice investors and sale bonds here in the United States.
3.     Does the Ethiopian Embassy have the legal mandate to promote the sale of bonds here in the United states without having the proper qualification or license to offer advice on such matters?
4.     If in fact there is no legal ground for the actions of the Embassy and the Ethiopian Government, what investigation and enforcements action will SEC be taking and will that be made public?
5.     Since we have planned to organize a public meeting to discuss on the legality of the sale of the Bonds will SEC be willing to send its officers and present its perspectives on the sale of the bonds to our constituents and the public at large?
6.     If the sale of the bonds was illegal what action will be taken to ensure that the sale will be stopped immediately (we learnt that there is a planned bond sale event organized in Chicago on April 27, 2013, hence, we demand immediate action on the matter)
7.     What legal action will SEC be taking to penalize those who were involved in the promotion and sale of the bond?
8.     What help will SEC be providing to those who wanted to retrieve their investment.

Taking into consideration the seriousness and urgency of the matter, we hope that that SEC will launch comprehensive investigation and take appropriate measures. Anticipating that SEC will give us immediate response, we want to use to indicate that we are prepared to collaborate with SEC in any required capacity and you may contact us at our contact number listed above.
Regards

Ethiopian Transitional Council Leadership
Post a Comment