Monday, April 29, 2013

ምቾት የሚባል በሽታ

1993 ክረምት፤ ለማትሪክ ፈተና ዝግጅት የማደርግበት ወቅት፡፡ ያኔ እንደብርቅ ከምናያቸ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ስጥ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑቱ የእረፍት ግዜያቸ የመሃል ሜዳ ///ሚካኤል //ቤት ባዘጋጀ የማትሪክ ማዘጋጃ መርሃ ግብር እኛን ተስፈኞቹን ይደግፉን ነበር፡፡ 
በትምህርት ክፍለ ግዜ መሃል ታዲያ የሃይማኖት ትምህርትም በደብሩ ሰባኪ ይሰጠን ነበር፡፡ ፈረንጆቹ ነፃ ግብዣ የለም/no free lunch/ እንደሚሉት ማለት ፡፡ እናም ፅድቅ ለነፍሱ የሻተ ሆነ ቀትን ለስጋ የፈለገ ስብከቱን ይከታተላል፡፡ እኔ ሁለቱም ጣፍጦኝ ስለነበር በንቃት ነበር የምከታተለ፡፡
ሰባኪ ደግሞ በጣም አሳታፊ ነበር፡፡ እሱ የሚለ ብቻ ሳይሆን እኛም የተረዳንን እንድንነግረ ያበረታታናል፡፡ እሱ ጌታ ማርያምን ‹‹አንቺ ሴት ከሳሾችስ የታሉ?›› አላት ካለ በኋላ ምን አላት?” ብሎ ይጠይቀናል፡፡ እኛም ንቁዎቹ  ከሳሾችስ የታሉ? አላት ስንል እንመልሳለን፡፡ ይሄኔ ይችም እውቀት ሆና እጅግ አድርጎ ያደንቀናል፡፡ እኛ እግዜርን እየፈራን እንጅ ምን አላት?” ሲለንአላት ብንል እንኳን የሚያደንቀን ይመስለኛል፡፡

Monday, April 22, 2013

ራስን በመውደድ ላይ ሳይሆን ሌሎችን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ዘረኝነት

በዩኔስኮ በተመዘገበ በኢሉ አባቦራ ዞን በሚገኘዉ የያዩ ደን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መረጃ ለጠየቃችሁኝና መረጃ ለሌላችሁ በሙሉ
እኔ ባለኝ መረጃ መሰረት አሁን እሳቱ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ነገር ግን ላለፉት 15 ቀናት ያክል በተለያዩ አካባቢዎችና አቅጣጫዎች እሳቱ እየተነሳና በአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ መልሶ እየጠፋ ነዉ የቆየ፡፡ ተከታታይ የሆነ እሳት አልነበረም፡፡ ላለፉት ጥቂት ቀናት ግን እሳቱ በመስፋፋቱ የመከላከያ ሰራዊትና የአካባቢ ነዋሪዎች በጋራ ተረባርበዉ አጥፍተውታል፡፡ የእሳቱ መንስዔ እስካሁን ባለ መረጃ ማር የሚቆርጡ ግለሰቦች እሳቱን እንዳስነሱት ነዉ የሚያመለክተ፡፡ ሆኖም በአካባቢ ባልተለመደ ሁኔታ ያጋጠመ የዝናብ መጥፋት ችግሩን አባብሶት ነበር፡፡ አሁን ግን ዝናብም መጣል ጀምሯል፡፡ 

Monday, April 15, 2013

የመለስ ዜናዊ ንግግር-የሕዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ በተጣለበት ወቅት

የተከበራችሁ የበአሉ ተሳታፊዎች፤
ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፤
የሳሊኒ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ሃላፊዎች፤
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች፤

ከሁሉ በማስቀደም በሀገራችን አዲስ ምዕራፍ በር ከፋች የሆነውንና በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው የሚሊኒየም ግድብ ስራ በይፋ በሚጀመርበት በአል ላይ ለመገኘት በመቻሌ የተሰማኝን ልዩ ክብርና ደስታ በራሴና በኢትዮጵያ መንግስት ስም ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ 

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በተሟላ ዝግጅት እንዲጀመር ሌት ተቀን በመረባረብ እዚህ ያደረሱትን ወገኖች ሁሉ በዚህ አጋጣሚ ለማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች፤
ክቡራንና ክቡራት፤

በታላቁ  የአባይ ወንዛችን ላይ በዛሬው እለት በይፋ መገንባት የሚጀምረው ግድብ የሚሊኒየም ግድብ መባሉ በብዙ ምክንያቶች ተመራጭ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የመጀመሪያው ምክንያት ግድቡ በአባይ ወንዝም ሆነ በሌሎች ወንዞቻችን ላይ ሊገነቡ ከሚችሉ ግድቦች ሁሉ የላቀውና ከፍተኛው ግድብ  በመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም በሚቀጥሉት አምስት አመታት ከፍተኛ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በመገንባት የራሳችንን የሃይል ፍላጎት በአስተማማኝ መልኩ ከማሟላት አልፈን ለጎረቤት ሀገሮች ሃይል በመሸጥ እድገታችንን ለማፋጠን የያዝነውን እቅድ ለማሳካት አይነተኛ ድርሻ ያለው ፕሮጀክት ስለሆነ ነው፡፡ በእቅዳችን መሰረት በሚቀጥሉት አምስት አመታት ከ 6 እስከ 8 ሺህ  ሜጋ ዋት ተጨማሪ ሃይል ለማመንጨት የተዘጋጀን ሲሆን የሚሊኒየም ግድብ ብቻ 5250 ሜጋ ዋት  በማመንጨት እቅዳችንን ለማሳካት ወሳኝ ድርሻ ይይዛል፡፡

Sunday, April 14, 2013

ተስፈኛዉ "መንግስት" የቦንድ ሽያጭን አወገዘ


በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በህመም ላይ ሳሉ ሃገራችን ገደል አፋፍ ላይ ቆማለችና እንታደጋት ብለዉ በአሜሪካ ምድር ኢትዮጵያን የሚገዛ አንድ ተስፈኛ መንግስት አቋቋሙ፡፡  ስመሙንም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር መንግስት ምክር ቤት አሉት፡፡  

ዛሬ ይህ የሽግግር ምክር ቤት ለዩናይትድ ስቴትስ ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ ኮሚሽን /SEC/ የፃፈዉ ደብዳቤ በአዉሮፓ ምድር ያሉ የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎችን አቋም ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነዉ፡፡ በአጭሩ የደብዳቤው ይዘት የህዳሴ ቦንድ የሚባል ነገር በአሜሪካ መሸጡ ይቁም፡፡ የገዙትም ገንዘባቸው ይመለስላቸዉ የሚል ነዉ፡፡

በውጭ ያሉት ተቃዋሚዎች በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የኢትዮጵያ ህዝብ ምርር ብሎ ሲያዝን ቢመለከቱት ጭንጋፍ የሕዝብ ርኩስ፤ የርጉም ዘመን ልጆች፤ የሬሳጀግና፤ ወዘተ… ሲሉ የስድብ መዓት አወረዱበት፡፡ የኛዉ አልበቃ ብሏቸዉ በፍርፋሪዋ የምታኖራቸውን ሀገር ከፍተኛ ዲፕሎማት ሱዛን ራይስን ዘለፉ፡፡ መለስን በተመለከተ በጎ የተናገሩትን ሁሉ ጥላሸት ለመቀባት ባለ በሌለ ሃይላቸዉ ተረባረቡ፡፡