Thursday, July 18, 2013

መንዜ ስነ-ቃሎች(ክፍል ሁለት)


ፀብ አጫሪ ስሞች በሚል በፃፍኩት ሀተታ ከጥቂት አመታት በፊት የተሰራ ጥናትን መሰረት በማድረግ የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳን የስም አወጣጥ ሁኔታ ለመቃኘት ሞክሬያሁ፡፡

በፅሁፉ ማጠቃለያም በክፍል ሁለት ፅሁፌ በአካባቢ ለወንጀል የሚያነሳሱ ስነ-ቃሎችንና ማጠቃለያ ሀሳቤን ይዤላችሁ እመለሳለሁ ብዬ ነበር፡፡ ይኸ በቃሌ ተገኝቻለሁ፤ በመጀመሪያ እነዚህን ስነ-ቃሎች ያንቧቸዉ፡፡

‹‹ባትገድል እንኳ በል እንገፍ እንገፍ
የአባትህ ጋሻ ትኋኑ ይርገፍ››፡፡

‹‹ገዳይ ገዳይ ያልሽው አባትሽ አይገድል
ገዳይ ገዳይ ያልሽው ወንድምሽ አይገድል
አርሶ ያብላሽ እንጂ ሆድሽ እንዳይጐድል››፡፡


‹‹እሱ ጀግና ነው ያለጥርጥር
ሳይገል አይመጣም በወጣ ቁጥር››፡፡

‹‹እንኳን በጠመንጃ እሳት በጐረሰው
ይገድላል በቡጢ ጀግንነት ያለው ሰው››፡፡

‹‹እጥፍጥፍ ባይ እንደ ኩታ ልብስ
አገዳደሉ አንጀት የሚያርስ››፡፡

‹‹እረ ዋርካ ሞኙ ሳያብብ ያፈራል
አንዱን ካልገደሉት አንዱ መች ይፈራል››

‹‹ድፋው ባፉ ከንብለው ባናቱ
እንደፈረደባት ታልቅስ ያቺ እናቱ››፡፡

‹‹አሻግረህ በለው ድፋው በግንባሩ
የገዳይ ሰፈር ነው አይነካም ክብሩ››፡፡
‹‹አገዳደሉ በልጅነቱ
ሳይፈታለት ዶቃው ካንገቱ››፡፡

‹‹ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደ አባቱ
አመልማሎ ስጡት ይፍተል እንደናቱ ››

 ‹‹ቁልቁለቱን ወርዶ ቦታው ሲደላደል
ይኸን ጊዜ ነበር ጠላትንስ መግደል››፡፡

‹‹ባልንጀሮችህ ገድለው ሲመጡ
ምን አቁሞሃል ከሰንበሌጡ
እኔም አልጋግር ያውልህ ሊጡ
አንሳና ጠጣው ከነወቂቱ››፡፡


ተጨማሪ ስነ-ቃሎችን ከፈለጉ ወደኋላ እመለስባቸዋለሁ፡፡
   
ለዚህ ፅሁፌ ያክል ስያሜንና ስነ-ቃልን አነሳሁ እንጅ የመንዝና አካባቢ ነዋሪዎችን ስነ-ልቦና በመወሰን ረገድ በርካታ ምክንያቶች መኖራቸ አይቀርም፡፡ ያም ሆነ ይህ መንዜዎች እንግዳ በመቀበልና በማክበር ያላቸን አኩሪ ባህል አለመግባባቶችን በትዕግስትና በሰጥቶ መቀበል መርህ በመፍታት ረገድ አልደገሙትም፡፡ ይልቁንም የ“ለምን እደፈራለሁ” እና “አትንኩኝ” ባይነት ባህሪያቸ ጎልቶ ይታያል፡፡

እኔ በወረዳ እየሰራሁ ባለሁበት ወቅት በ5 ሳንቲም የተነሳ የሰ ህይወት ጠፍቷል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነዉ፡፡ ሰ ጠጅ ሲጠጣ ቆይቶ ከአስተናጋጁ ጋር በሒሳብ ይጣላሉ፡፡ 5 ሳንቲም ጨምር አልጨምርም ክርክር ይነሳል፡፡ የሁለቱ ንትርክ ያሰለቸ ከጎን ያለ መሸተኛ ለአስናጋጁ “በቃ ተወ፤ ደሞ ለ 5 ሳንቲም፤ እኔ እጨምርልሃለሁ” ይላል፡፡ በዚህ ግዜ ባለጉዳዩ “እኔ አጥቼ ነ እንዴ አንተ የምትከፍልልኝ?” በሚል ክርክር ያነሳል፡፡ ለምን ተደፈርኩ ነ እንግዲህ፡፡ ነገሩ እየከረረ ይሄድና በያዘ ዱላ አናቱን ሲለ ነገር ለማብረድ ብሎ የገባ ሰ ሂወት እዛ አለፈች፡፡

በነገራችን ላይ የመንዝ አርሶአደሮች የሚይዙት ዱላ አያዳግምም፡፡ አንድ ምት ለአንድ ነፍስ በቂ ነ፡፡ ስድብ ደግሞ አይመቻቸም፡፡ ከተጣላሃቸና ፊታቸዉ ከቆምክ ያቀምሱሃል፡፡ ሳይቀድምህ መቅደም የሚሉት ብሂል አላቸዉ፡፡ የኔ ሃገር ሰ ወደ ደቡብ ሄዶ ሰዎች በጃቸዉ ድንጋይ ይዘ ሲሰዳደቡ ቢሰማ “በሞኝነታቸዉ” መሳለቁ አይቀርም፡፡

ስለ መንዞች ዱላ ካወሳሁ ዱላና መንዜ ያላቸን ግንኙነት ማንሳት ግድ ይለኛል፡፡ የመንዝ አርሶ አደርና ዱላ ለአፍታም አይለያዩም፡፡ በእርሻ ቦታ፤ በሃዘን ቤትም ሆነ በሰርግ ቦታ ሁሉ ከእጁ ዱላን አይለያትም፡፡ ቅቤ እየቀባ ጭስ እንድትጠግብ ጣሪያ ላይ ይሰቅላታል፤ በቆዳ ይለብጣታል፤ ብረት ዙሪያዋን ይጠመጥምላታል /ጅንፎ ይሉታል/፡፡ በሚስትና በዱላ ቀልድ የለም ይላል ሲያሞካሻት፡፡ መንዜ ከልብ ለሚወደዉ “ቆንጆ” ዱላ በስጦታ ያበረክታል፡፡ እኔም ጥቅም ላይ ባላውለውም ቆንጆ ዱላ ቤቴ አስቀምጫለሁ፡፡

አንድ ወቅት በገበያ ቀን /ቅዳሜ/ በመጠጥ ቤቶች በሚነሳ ተራ ግጭት የሰ ህይወት በተደጋጋሚ መጥፋቱ ያሳሰባቸዉ የወረዳ ፖሊሶች አንድ ስልት ነደፉ፡፡ አርሶ አደሮች ወደ ከተማ በሚገቡባቸዉ በሮች በመጠበቅ ጠዋት ዱላቸን እየመዘገቡ በአደራ መረከብና ማታ ሲመለሱ መስጠት፡፡ የአርሶ አደሮቹን ሎ “ከዱላ ነፃ” በማድረግ ሰላም ለማስፈን ታስቦ ነበር፡፡ መንዜዎቹ ግን ከአንድ ሳምንት በላይ “አልተሸወዱም”፡፡

ከገበያ ቀናት ጭ ወደከተማ ሲመጡ ሁለት ዱላ ይዘ ይመጡና አንዱን ቅዳሜ “እንዲጠቀሙበት” ከዘመድ ወይም ከመጠጥ ቤት አስቀምጠዉ ይመለሳሉ፡፡ በሌላ ቀን ለገበያ ሲመጡ በእጃቸዉ የያዙትን ዱላ ከከተማዋ በር ለፖሊስ ያስረክቡና ከተማ ገብተዉ ያስቀመጡትን ዱላ ይዘ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ማታ ደግሞ ተቀያሪ ዱላቸን አደራ ቤታቸ አስቀምጠ ታስሮ የዋለዉን ዱላቸን በማስፈታት ‹‹ ኧረ ጥራኝ ጫካ አረ ጥራኝ ዱሩ፤ ላንተም ይሻልሃል ብቻ ከማደሩ›› እያሉ ወደ ቤታቸ ያዘግማሉ፡፡

መግቢያ በር ላይ ዱላቸን የነጠቋቸን ሰዎች ከተማ ዉስጥ ዱላ ይዘ ቢያዩአቸ ግራ የተጋቡት ፖሊሶች ሚስጥሩን ሲረዱ ከክትትልና ቁጥጥር ያለፈ ሌላ መፍትሄ ማፈላለግ ጀመሩ፤ የማህበረሰብ አቀፍ የወንጀል መከላከል መርሃ ግብር፡፡

በዚህ መርሃ ግብር በተሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች አሁን የአመለካከት ለጥ መምጣት ጀምሯል፡፡ በአካባቢ የእርስ በርስ ግድያዎች ቁጥርም በተከታታይ መቀነስ እየታየበት እንደም ወረዳዉ በወንጀል መከላከል አርዓያ እየሆነ ነዉ፡፡

ሆኖም አሁንም ቢሆን በስነ-ቃሎቹ እንደሚታየዉ ጀግንነትን ከሰ መግደል ጋር አንድ አድርጎ የመገንዘብና ሴትነትን የሽንፈትና የበታችነት ምልክት አድርጎ የመሰድ ችግር አለ፡፡ ይህን ለመቀየር ከማህበረሰብ አቀፍ የወንጀል መከላከል ትምህርቶች በተጨማሪ የስርዓተ ፆታና ግብረ ገብ ትምህርትን ማስፋፋትን ግድ ይላል፡፡

አመጽን፣ ዝርፊያን፣ ሰው መግደልን፤ በጥቅሉ ወንጀልን የማይወድ፣ እነዚህን ክፉ ተግባራት የሚዋጋና፣ የተጣሉትን የሚያስታርቅ፣ የተበደሉትንም የሚያስክስ፣ ለአካባቢው ሰላም፣ ብልጽግናና ለህዝብ ደህንነት የሚያስብና ለልማት ስራዎች ግንባር የቀደመ ሁሉ ጀግና ሊባል ይገባዋል፡፡

እንደነዚህ አይነት ሰዎችን ባለስልጣናት፣ የህዝብ ማህበራት በአጠቃላይም ህብረተሰቡ ጀግና እያሉ ሊያሞግሷቸው፣ ሊሾሟቸውና ሊያከብሯቸው ይገባል፡፡

ተጨማሪ 16 ስነ-ቃሎችን ከታች ተመልከቱ፡፡
 ‹‹የገዳይ ወዳጅ ታስታውቃለች
አፋፍ ላይ ሆና በለው ትላለች
የፈሪ ወዳጅ ታስታውቃለች
አፋፍ ላይ ቆማ ተዉ ሽሽ ትላለች››፡፡

‹‹ከጥንት ነው ከምሰሷቸው
አባቱ ገዳይ ደግሞ ልጃቸው››፡፡

 ‹‹ተኳሽ እወዳለሁ ገዳይም አልጠላ
ሲደክመኝ አርፋለሁ በጐፈሬው ጥላ››፡፡

<<ከኮርቻው ላይ አድርገው ውድም
ለአንተ መኖሪያ አገር አይገድም>>፡፡

‹‹ቤልጅግ አለቀሰ  ስቅስቅ ብሎ እንደሰው
አልጋ ላይ ተጋድሞ ትኋን እየላሰው››፡፡

‹‹ቢቸግር ነው እንጂ ጐመን እራት ነወይ?
የእነአጅሬው አገር ጎራው ደህና ነወይ››?

‹‹ቁና ጤፍ ፈሶብኝ ስለቅም ሳስለቅም
ሰው የአባቱን አገር ካልገደለ አይለቅም››፡፡

‹‹እርሳሱ ጥቁር ምላሱ መንታ
ቆላ ተኩሶ ደጋ የሚመታ››፡፡
‹‹በቦንብ ገዳይ በድቡልቡሉ
በሽጉጥ ገዳይ በስንዝር ሙሉ
የአባቱ አሽከር አሞተ ሙሉ››

‹‹አካለ ቀጭን እግረ ወንበዴ
ይቆራርጣል በስል ጐራዴ››፡፡

‹‹በዚያው ወርዶ በዚያው ተራምዶ
አቆላላፊ የሬሳ ነዶ››፡፡

‹‹ኧረ ጠራ ሰማይ ምድር ደፈረሰ
የጠላት መሞቻው ቀኑ እየደረሰ››

‹‹አባቶቻችን የድሮዎቹ
ለመግደል እንጂ ለሞት አይመቹ››!!

‹‹የጠላቴ አንገት ምኑ ተረፈ
ተቆርጦ ተቆርጦ ተረፈረፈ!››

‹‹ስጡኝ ምንሽሬን ቢለየኝ አልወድም
ደም ከፈሰሰ ነው የሚደርሰው ወንድም››፡፡

‹‹ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደአባቱ
አመልማሎ ስጡት ይፍተል እንደናቱ ››

Post a Comment