Friday, February 15, 2013

በጥንቃቄ ጉድለት የተከሰቱ ግድያዎች

ከአስራ ስምንት አመት በታች ያሉ እንዲያነቡት አይፈቀድም፡፡ በተለይ ወላጆች ግን እንድታነቡት ትበረታታላችሁ፡፡

በዛሬው ፅሁፌ በጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ በህፃናት ላይ የደረሱ ሶስት የሞት አደጋዎችን አስነብባችኋለሁ፡፡ ከዛ በፊት ግን ባለፈዉ ፅሁፌ ቃል የገባሁላችሁን ያልተሳካውን የጭካኔ ግድያ ሙከራ ታሪክ ልንገራችሁ፡፡

የዉ ሃብታም ቢጤ ነዉ፡፡ ገንዘብ ቢሞላለትም ግን ጉልበቱና አይኑ ደክሟል፡፡ የሚኖረዉ ደግሞ ከሰራተኛ ጋር ብቻ ነዉ፡፡ 

አንድ ቀን እሱ ጓዳ እያለ ሰራተኛዋ ሌላ ሰዉ ጋር ደዉላ በአፍ መፍቻ ቋንቋዋ ትነጋገራለች (ቋንቋን ነግረዉኛል፤ ለፅሁፌ የሚጨምረዉ እሴት ስለሌለ ግን አልጠቀስኩትም)፡፡ ሰዉየ የሷን ቋንቋ መስማት የሚችል አልመሰላትም፡፡ እርሱ ግን ያለችን ሁሉ ልቅም አድርጎ ሰምቶ ነበርና ዘወር ብሎ ለፖሊሶች ይደላል፡፡

ፖሊሶቹ ቤቱን ከተቆጣጠሩ በኋላ “አሁን የደወልሽበት መልሰሽ ደይና ቶሎ ብላችሁ ኑ በያቸ ብለ ያስገድዷታል፡፡ እርሷም እንደተባለች ታደርጋለች፡፡ አፍታም ሳይቆዩ ሰዉየን ገድለዉ ንብረቱን ለመዝረፍ የተቀጠሩ ሰዎች መኪና ይዘ ሲመጡ በፖሊስ ቀለበት ስጥ ወደቁ፡፡

አሰቃቂ ስህተት አንድ

ይህንን የነገረችኝ ደግሞ የአክስቴ ልጅ ነች፡፡ ባለፈ በነገርኳችሁ የተሲያት ቡና ላይ ማለት ነ፡፡ 

እናት ሆዬ ልጇን ጡት ካጠባች በኋላ እንቅልፍ እያዳከመ መሆኑን ስታይ ሰራተኛዋን ጠርታ “አጎበሩ ዉስጥ አስገቢና አስተኚዉ” ብላ የቤት ዉስጥ ስራዋን ትቀጥላለች፡፡ 

ስራ ስራዋን ስትል የቆየችዉ እናት ታዲያ የልጇ ድምፅ ጥፍት ሲልባት ወደ አልጋ ሄዳ ስታይ አጣች፡፡ ሰራተኛይቱን ጠርታ “ልጁ የታለ?” ብላ ጠየቀቻት፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ከገጠር የመጣችዉ ሰራተኛ ታዲያ “እዛ ዉስጥ ነ አለቻት ወደ ፍሪጁ እያሳየች፡፡ ሰራተኛይቱ በደንብ ባለመስማት ይሁን ወይም አጎበርና ፍሪጅ ተመሳስሎባት/ተምታቶባት ልጁን ወስዳ የከተተችዉ ማቀዝቀዣ /refrigerator/ ስጥ ነዉ፡፡ ህፃኑ ከፍሪጁ ሲወጣ ሂወቱ አልፋለች፡፡

አሰቃቂ ስህተት ሁለት

ይህን መሰል ታሪክ ባለፈዉ አመትም አንዲት ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ የምትዘግብ ጓደኛዬ ነግራኝ ነበር፡፡ ታሪኩ በጋዜጣ ይታተም ይቅር አላዉቅም፡፡ 

አዲስ አበባ ስጥ ነዉ፡፡ እናትየዋ ወደ ስራ ከመሄዷ በፊት አዲስ ለቀጠረቻት ሰራተኛ ጡጦን እያሳየቻት “ህፃኑን አጥቢና ፍሪጅ ዉስጥ አድርጊዉ” ትላታለች፡፡ ወተቱ እንዳይበላሽ መሆኑ ነዉ፡፡ ሰራተኛይቱም የተባለችን አደረገች፡፡ ግን ጡጦን ሳይሆን ህፃኑን ነበር ፍሪጅ ዉስጥ የከተተች፡፡ እናም ልጁ ሞተ፡፡

ይህን ታሪክ በነገረችኝ ሰሞን እኔም አንዲት የዘመዴን ልጅ ህፃን ልጄን እንድታግዘኝ ብዬ ከገጠር አምጥቻት ነበር፡፡ የከተሜነት ኑሮ ሲያልፍ አልነካትም፡፡ የተንቀለቀለ የኤሌክትሪክ ምድጃ /stove/ በእጇ ለማጥፋት የምትሞክር ነች፡፡ የዋህና ግትር ነች፡፡ አታድርጊ የተባለችዉን ነገር ደግሞ ካልሞከረች አይነጋላትም፡፡

ጓደኛዬ ይህን ታሪክ የነገረችኝ ዕለት ማታ ቤት ስገባ ዘመዴን ጠራኋትና “ይሄ ፍሪጅ ነዉ፡፡ ስጡ የሚገባው ምግብና መጠጥ ብቻ ነ፡፡ ሚጣን እንዳታስገቢያት እሺ” ስል መከርኳት፡፡ እሷም “እሺ” አለች፡፡

በማግስቱ ቢሮዬ ስገባ ነፍሴ ተጨነቀች፡፡ የልጅቱ ባህሪ ትዝ አለኝ፡፡ አታድርጊ የተባለችዉን መሞከር ትፈልጋለች፡፡ አንድ ቀን ልጄን ፍሪጅ እንዳትከትብኝ ተጨነቅሁ፡፡ እየሰጋሁ አልኖርም ብዬ ወደአመጣሁባት በክብር መለስኳት፡፡

አሰቃቂ ስህተት ሶስት

ለአክስቴ ልጅ ግን እንዲህ አይነት አሟሟቶች በተለይ በህፃናት ላይ የሚከሰቱት ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ ብቻ ሳይሆን የኛ የወላጆች ሃጢያት እንደ ሰዶምና ገሞራ ሰዎች ስለበዛ ነዉ፡፡ “ሰራተኞች ምን ያርጉ፡፡ የእግዜር ቁጣ ነዉ፡፡ የኛ ሃጢያት በዝቷል” አለች፡፡ 

“ታዲያ ሃጢያታችን ሞልቶ ባይፈስ ኖሮ አህያ ሰን ይበላ ነበር?” ብላ አፈጠጠችብኝ፡፡ ወይ ጉድ፤ ደሞ ምን ልታመጣ ነ ብዬ አይን አይኗን አያት ጀመር፡፡ 

ከሻሸመኔ ወጣ ባለች ከተማ ነ አለች፤ እናት ህፃን ልጇን የጠዋት ፀሃይ እያሞቀች ሰነቱን ቅቤ ትቀባዋለች፡፡ በደንብ እያሻሻች ሰዉነቱን ካፍታታችለት በኋላ ባለበት ትታ ወደ ቤቷ ትገባለች፡፡ ለመመለስ አፍታም አልቆየች፡፡ የልጇን ነፍስ ለመታደግ ግን እጅግ ዘግይታለች፡፡
ስትመለስ ያገኘችው የልጇን ጭንቅላት ብቻ ነበር፡፡ “እዛዉ በር ላይ ታስሮ የነበረ አህያ ህፃኑን እንደ ካሮት ቁርጥምጥም አድርጎ በልቶታል” አለችኝ፡፡ ከአክስቴ አነጋገር ውስጥ ጨካኝነት ታየኝ፡፡ የባሰ ጉድ ሳይመጣ ቡናዬን ጨልጨ ወጣሁ፡፡

ወላጆች ሃጢያታችን ይብዛም ይነስ ለልጆችችን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡ ቢያንስ እንዲህ አይነት በጥንቃቄ ጉድለት የሚመጡ አደጋዎችን መቀነስ እንችላለንና፡፡ ግድ ሆኖ እንጅ ልጅንማ ማን እንደራስ ይይዛል?

ለብዙዎቻችን እዚህ አዲስ አበባ በደላላ አማካኝነት የምናገኛቸዉ ሰራተኞች የሚያቀርቡት ቅድመ ሁኔታ ከአቅማችን በላይ ይሆንብናል፡፡ ቤታችሁ ውስጥ ልብስ ማጠቢያ ማሽን፤ ፍሪጅ፤ ዲቪዲ፤ ወዘተ… አለ ወይ? ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ህፃን ልጅ ካለ ደግሞ መግባትም አይፈልጉም፡፡ እሺ ቢሉ እንኳን ክፍያቸዉን ጣራ ላይ ይሰቅሉታል፡፡

እናም አጋጣሚዉ ካለን ከገጠር ዘመዶቻችን ሰራተኛ እናመጣለን፡፡ ይህ ግን የራሱ ችግር እንዳለዉ ከላይ የጠቀስኳቸዉ አብነቶችና ሌሎች መለስተኛ ችግሮቻችን ያሳያሉ፡፡ እንደ ትራፊክ አደጋና በኤሌክትሪክ መያዝ ያሉ ሌሎች ችግሮችም በራሳቸው ከገጠር በመጡ ሴቶች ላይ በተደጋሚ ይከሰታሉ፡፡ 

ስለሆነም በሃላፊነት ያመጣናቸውን /የቀጠርናቸዉን/ ሰራተኞች የማስተማር፤ የማሰልጠንና ከአዳዲስ አሰራሮች ጋር የማስተዋወቅ ሃላፊነት አለብን እላለሁ፡፡ ያኔ የልጃችንም፤ የሰራተኛችንም በጥቅሉ የቤተሰባችን ደህንነት ይረጋገጣል፡፡

የሻሸመኔ ጉዞዬን ተንተርሼ በተከታታይ ሁለት ፅሁፎች ያነሳሁትን ሃሳብም በዚሁ ቋጨሁ፡፡
Post a Comment