Thursday, February 28, 2013

ህልም ፈርተን ሳንተኛ አናድርም“ለዘመናት በአባይ ውሃ ሙላት በጎርፍ ሲጥለቀለቁ የነበሩ አካባቢዎች በተለይም የሱዳን አካባቢዎች ይህ ግድብ ሲጠናቀቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከአደጋው ነጻ ይሆናሉ፡፡” ይህን ያሉት ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ነበሩ::

የሳዉዲ አረቢያ ም/ል መከላከያ ሚኒስትር ካሊድ ቢን ሱልጣን ደግሞ ከሰሞኑ ግብፅ ሄደዉ “የህዳሴዉ ግድብ ምናልባት ከፈረሰ የተገደበዉ ዉሃ ሲፈስ ካርቱምን ያጥለቀልቃታልእንዲያዉም ለአስዋን ግድብም ይተርፋል”  አሉ:: 

ይሄማ የፈሪ ትንቢት ነዉ:: “አንድ ቀን ቢፈርስስ?” ብላ ግብፅ አስዋንን ከመገደብ ወደኋላ አላለችም፤ ሱዳንም ሮሳሪስን እንዲሁ:: 

ቦሊቪያዉያን የሞት መንገድ ብለዉ በሰየሙትና በየአመቱ በአማካኝ 250 ያክል ሰዎችን በሚገድለዉ የገደል ላይ መንገድ መኪና ማሽከርከራቸዉን አልተዉም:: ወደ አማዞን ለመሄድ  እሱን ማለፍ የግድ ነዋ::

Monday, February 25, 2013

ዉሸታሞችስ ኢቲቪን ዉሸታም የሚሉቱዉሸታሞችስ ኢቲቪን ዉሸታም የሚሉቱ ናቸዉ፡፡ 

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ አላደገም ብለው ሽምጥጥ አድርገው የካዱ የኢቲቪ የልማት ዘገባ እንዴት እውነት ይሆንላቸዋል?

በባሌም በቦሌም ብለዉ የመንግስትን ስልጣን መያዝ ሲፈልጉና ይህም የጥፋት በር ክርችም ተደርጎ የተቆለፈባቸው ሃይሎች የኢቲቪ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዜናዎች እንዴት እውነት ይሆኑላቸዋል?

ፅንፈኛ አሸባሪዎች በየጓዳዉ የሚያቦኩትን በአደባባይ የሚያጋልጠው የኢቲቪ ዘገባና የመንግስት የፀረ-ሽብር ዘመቻ እንዴት እውነት ይሆንላቸዋል? 

Sunday, February 17, 2013

የሼክ ሻኪር ምክር፤ የጦርነት ቅስቀሳ ወይስ የሰላም ጥሪ?ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ-ገፆች አነጋጋሪ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ በትዉልድ ግብፃዊው በዜግነት አሜሪካዊዉ ኢማም ሼክ ሻኪር በዋሸንግተን ዲሲ በተካሄደ “የድምፃችን ይሰማ” አንደኛ አመት በዓል ላይ ያደረጉት ንግግር ነዉ፡፡

ቪዲዮዉ ለእይታ ከበቃ ጀምሮ በርካቶች በተለይ በፌስ ቡክ ላይ “ሃገራችንን ለስልታዊ ጠላታችን (ግብፅ መሆኗ ነዉ እንግዲህ- እኔ እንኳን ይችን አላምንባትም) አሳልፈዉ የሰጡ ከሃዲዎች” በማለት አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡ ለዚህም መነሻቸዉ መድረክ መሪዉ ተናጋሪዉን ሊጋብዝ ሲል “እኛ (በዉጭ ያሉ የድምፃችን ይሰማ ንቅናቅ ደጋፊዎችን ማለቱ ነዉ) ገና ከጅምሩ ችግር ሲያጋጥመን የሳቸዉን ምክር ለመጠየቅ ሄድን፡፡ እሳቸዉም ከ‘ሀ’ አስከ ‘ፐ’ የምንጓዝበትን መንገድ ነገሩን” ማለቱ ነዉ፡፡

ሼክ ሻኪር ለ27 ደቂቃ በቆየዉ ንግግራቸዉ በኢትዮጵያ የዉስጥ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዉስጥ ሰተት ብለዉ መግባታቸዉን አረጋግጠዋል፡፡ በተደጋጋሚም አመፅን የችግር መፍቻ አድርገዉ ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ በርግጥ መድረክ መሪዉ መጨረሻ ላይ ብቅ ብሎ ‘ልብ በሉ፤ አመፅን ግን እየሰበኩን አይደለም’ የሚል ማስተባበያ ቢጤ ቢሰጥም ሰዉየዉ የሚፈልጉትን ብለዋል፡፡

Friday, February 15, 2013

President Isaias's interview

President Isaias Afwerki of Eritrea made his first tv interview regarding the 21 January 2013 mutiny.

President Isaias Afwerki said that the ‘21 January 2013 incident’ was, and is no cause at all, for apprehension and that the Government opted to remain silent regarding the matter so as to give no ground for the authors of sheer lies. The President told Erina that it was natural for the Eritrean people inside the country and abroad to seek information about the situation since the very hours of the incident out of patriotic concern.

it is just a childish interview.

በጥንቃቄ ጉድለት የተከሰቱ ግድያዎች

ከአስራ ስምንት አመት በታች ያሉ እንዲያነቡት አይፈቀድም፡፡ በተለይ ወላጆች ግን እንድታነቡት ትበረታታላችሁ፡፡

በዛሬው ፅሁፌ በጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ በህፃናት ላይ የደረሱ ሶስት የሞት አደጋዎችን አስነብባችኋለሁ፡፡ ከዛ በፊት ግን ባለፈዉ ፅሁፌ ቃል የገባሁላችሁን ያልተሳካውን የጭካኔ ግድያ ሙከራ ታሪክ ልንገራችሁ፡፡

የዉ ሃብታም ቢጤ ነዉ፡፡ ገንዘብ ቢሞላለትም ግን ጉልበቱና አይኑ ደክሟል፡፡ የሚኖረዉ ደግሞ ከሰራተኛ ጋር ብቻ ነዉ፡፡ 

አንድ ቀን እሱ ጓዳ እያለ ሰራተኛዋ ሌላ ሰዉ ጋር ደዉላ በአፍ መፍቻ ቋንቋዋ ትነጋገራለች (ቋንቋን ነግረዉኛል፤ ለፅሁፌ የሚጨምረዉ እሴት ስለሌለ ግን አልጠቀስኩትም)፡፡ ሰዉየ የሷን ቋንቋ መስማት የሚችል አልመሰላትም፡፡ እርሱ ግን ያለችን ሁሉ ልቅም አድርጎ ሰምቶ ነበርና ዘወር ብሎ ለፖሊሶች ይደላል፡፡

Sunday, February 10, 2013

ሶስት የጭካኔ ግድያዎች

ከአስራ ስምንት አመት በታች ያሉ እንዲያነቡት አይፈቀድም፡፡ በተለይ ወላጆች ግን እንድታነቡት ትበረታታላችሁ፡፡

ሻሸመኔ ከተማ የምትኖር በጣም የምወዳት ግን ከኔ በላይ እሷ የምትወደኝ አክስት አለችኝ፡፡ አንዲት ልጅ፤ ስምንት የልጅ ልጅና አንድ የልጅ ልጅ ልጅ አላት፡፡ እድሜዋ እየገፋ ነዉ፤ ህመምም በየግዜው እየተመላለሰ ይጎበኛታል፡፡

ከሶስት ወራት በፊት በስራ ምክንያት ሃዋሳ ስሄድ እግረመንገዴን ጠይቄያት ነበር፡፡ ሰሞኑን ታዲያ ደውላ “አንድ ግዜ እንኳን ናና አይንህን ልየ፤ በጣም እያመመኝ ነ አለችኝ፡፡ እኔም የሶስት ቀን ፈቃድ ጠይቄ ሄድኩላት፡፡ ፈጣሪ ይመስገን ስሄድ ግን ተሸሏት አገኘኋት፡፡

ከልጇ ቤት ሄጄ ሳለ ቡና ተፈልቶ ወሬው ደራ፡፡ አንድ ጥያቄ አነሳሁ፡፡ “ከወር በፊት እዚህ ከተማ ከነልጆቿ ስለተገደለችሴት እስኪ ንገሩኝ” አልኳቸው፡፡

Wednesday, February 6, 2013

ጅሃዳዊ ሐረካት፡ ክፍል ሁለት

“ጅሃዳዊ ሓረካት” አየነዉ፡፡

ፊልሙ የጀመረዉ ሽብርተኝነት በአለም አቀፍ፤ በአህጉር አቀፍና በክፍለ-አህጉር ደረጃ ያለዉን አዝማሚያ፤ የሽብርተኝነት ምንጮችንና የሚከተላቸዉን ተለዋዋጭ ስልቶች በማስቃኘት ነዉ፡፡ ያለፉትን ሁለት አስርት አመታት በፅኑ እንቅልፍ /hibernation/ ዉስጥ ካላሳለፍን በቀር ይህን በ“እዉነት”ነት ለመቀበል የሚከብደን አይመስለኝም፡፡
መሃሉ ተከድኖ ይብሰልልን፤ ኋላ አንመለስበታለን፡፡

በፊልሙ መዉጫም “እዉነት” ነዉ ከሚል መደምደሚያ ላይ እንዳንደርስ የሚያግደን ነገር የለም፡፡ መዉጫዉ በእድገት አዙሪት ዉስጥ መግባቷ በሁሉም አፍ ስለተነገረላት ኢትዮጵያ ዳግም ከማዉራት ያለፈ ነገር አልነበረዉም፡፡ ትረካዉን ደግፎ የቀረበዉ ምስልም ቢሆን ቀድሞም በሃገራችን ያየንዉ የልማት ስራ ነዉ፡፡ የኢንዱስትሪ፤ የግብርና፤ የመሰረተ ልማት መስፋፋት፤ ወዘተ… እዚህ ያለነዉ ዜጎች በአይናችን ጭምር ያየነዉ ነዉ፡፡ በርግጥ ልዩነቱ ጥቂት እጆች የፈንጂ ጉድጓድ ሲቆፍሩ በፊልሙ ማየታችን እንጅ ሚሊዮን እጆች የችግኝ መትከያ ጉድጓዶችን ሲቆፍሩም በፊት አይተናል፡፡ 
         
እናም የፊልሙን ዳርናዳር ተቀብለን በመሃሉ ምንነት ላይ ለመወሰን የመመልከቻ መነፅራችንን እናስተካክል እላለሁ፡፡ በኔ እምነት የ ‘እዉነታ/ድራማ’ እንካሰላንቲያዉ መፍቻ በፊልሙ ላይ ምስክርነታቸዉን በሰጡ ተጠርጣሪዎች ላይ ባለን እይታ ብቻ ሊፈታ ችላል፡፡ የአክራሪዎች፤ የመንግስት ወይም የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የኋላ ታሪክ የፊልሙን ምንነት በመወሰን ረገድ ያላቸዉ ድርሻ ወደ ዜሮ ተጠግቷል፡፡

Tuesday, February 5, 2013

ጀሃዳዊ ሐረካት፡ እዉነታ ወይስ ድራማ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዛምቢያ አቻዉ ጋር ያደረገዉን ጨዋታ የኳስ አፍቃሪዎችም ሆኑ ለኳሱ ደንታ የሌላቸዉ ኢትዮጵያዉያን በናፍቆት ሲጠብቁት ከርመዉ በጉጉት ኮምኩመዉታል፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በኢቲቪ1 ዛሬ ምሽት ሊያስተላልፍ ያሰበዉ ፕሮግራምም በዚሁ መልኩ በጉጉት እየተጠበቀ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡

ይህን ፕሮግራም ኢቲቪ “እዉነታ” ሲለዉ ‘መንግስት በእስልምና እምነት ላይ በደል እየፈፀመ ነዉ’ የሚሉ ወገኖች ደግሞ “ድራማ” ብለዉታል፡፡
ያም ሆነ ይህ ኢሬቴድ የአሸባሪዎችን ሴራ ፍንትዉ አድርጎ የሚያሳየዉን ፕሮግራም ጥር 28 አስተላልፈዋለሁ ብሎ ማስታወቂያ ከለቀቀ ጀምሮ በማህበራዊ ድረ-ገፆችም “ኢቲቪ ድራማዉን ማክሰኞ ምሽት ያሳያል” የሚሉ ተጨማሪ ማስታወቂያዎች ተበራክተዋል፡፡ የኢቲቪ “እዉነት ነዉ” እና የዛኛዉ ጫፍ “ዉሸት ነዉ” እንካሰላንቲያ ፕሮግራሙን በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡