Saturday, January 12, 2013

መለስ ዜናዊ በአሌክስ ዲ ዋል ዕይታ

መለስ ዜናዊን ለምትወዱት ወይም ለምትጠሉት ብቻ፡፡ መሃል ሰፋሪዎች እንኳን ቢቀርባችሁም ግድ የለም፡፡ እናንተ መለስን የምትወዱ ወይም የምትጠሉ ግን እርሱን ስታደንቁም ሆነ ስትጠሉት አዉቃችሁት ቢሆን ያምርባችኋል፡፡ መለስን በደንብ አድርገዉ ከሚያዉቁት አለም አቀፍ ስብዕና ካላቸዉ ሰዎች አንዱ አሌክስ ዲ ዋል ነዉ፡፡ ይህ ብሪታኒያዊ መለስ ከበረሃ እስከ ቤተመንግስት ያለዉን ስብዕና በተከታዩ በጣም አጭር ፅሁፍ አብራርቶታል፡፡ 

ለነገሩ እርሱ ስለ መለስ የፃፈዉ ይህን ብቻ አይደለም ፡፡ ይችኛዋን ስታነቡ ግን አሌክስ ዲ ዋል ‘ከወደደ ወደደ፤ ከጠላ ጠላ’ የሚሉት አይነት ሰዉ እንዳልሆነ ትረዳላችሁ፡፡ ከአንድ ነገር ዉሰጥም ቢሆን የሚወደዉንና የሚጠላዉን ለይቶ የሚያዉቅ ነዉ፡፡ እሱ የወደደዉ ወይም የጠላዉ ሁሉ ግን ትክክል ነዉ እያልኩ አይደለሁም፡፡

አሌክስ ፀሃፊና ተመራማሪ ነዉ፡፡ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በሱዳንና ደቡብ ሱዳን ላይ ጥልቅ ምርምር ያካሄደ ምሁር ነዉ፡፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካም ከደርግ ግዜ ጀምሮ እስከ ሽግግሩ ወቅት ድረስ አብጠርጥሮ ያዉቀዋል፡፡ አሁን የወርልድ ፒስ ፋዉንዴሽን ዳይሬክተር ሲሆን የተለያዩ አለምአቀፍ ሃላፊነቶችም አሉት፡፡ አሜሪካ በሶማሊያ ዉስጥ አድርጋዉ የነበረዉን ወታደራዊ ጣልቃገብነትና አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሱዳኑ ፕሬዝዳንት ላይ የቆረጠዉን የእስር ማዘዣ አምርሮ የተቃወመ ነዉ፡፡ 

አሌክስ ይህን ፅሁፍ ከኢትዮጵያዊዉ አብዱል መሃመድ ጋር በመሆን ነዉ ያዘጋጀዉ፡፤ አብዱል ሞሃመድ በአፍሪካ ህብረት የሱዳን ጉዳይ ከፍተኛ የአስተግባሪዎች ፓነል ሃላፊ ነዉ፡፡ የነዚህን ሁለት ጎምቱ ምሁራንን ፅሁፍ ማንበብ መለስ ዜናዊን አዉቆ ለማድነቅ ወይም ለመቃወም ያግዛል ብዬ አሰብኩ፡፡ እነሆም ሼር አደረግሁላችሁ፡፡   
Post a Comment