Tuesday, January 29, 2013

ግልፅ ደብዳቤ ለጆን ኦቢ ሚኬል


ቀንደኛ የቸልሲ ደጋፊ ነኝ፡፡ ቸልሲ በ2008 በማንቸስተር ዩናይትድ ተሸንፎ ዋንጫዉን ሲነጠቅ ራቴን ሳልበላ አድሬያለሁ፡፡ በማግስቱም የምግብ ፍላጎቴ መዘጋቱን አልረሳዉም፡፡ አምና ባርሴሎናን አሸንፎ የቻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ ደግሞ ፊቴ በደስታ እንባ ታጥቧል፡፡ ሞሪንሆ ከክለባችን ሲሸኝ ሰማይ የተደፋብኝ ያክል ደንግጬ ነበር፡፡ /ይህን ደብዳቤ ከፃፍኩ በኋላ ተመልሷል፡፡/

እዉነቱን ልንገርህና ሌሎቹን ቀርቶ አዳነ ግርማንና ሳላዲን ሰይድን እንኳን በመልካቸዉ ለይቸ አላዉቃቸዉም /አሁን እንኳን እየለየኋቸው ነው/፡፡ አንተ ግን ስትከሳና ስትወፍር እንኳን ለዉጥህን በሚገባ እለየዋለሁ፡፡ አንተ ታክል ገብተህ ተቃራኒህን ስትጥለዉ ሰዉነቴ በድንጋጤ ይሸማቀቃል፡፡ ለወደቀዉ አዝኜ ሳይሆን ትንሽ ጫር አድርጎህ ተም እንዳትጎዳ እየሰጋሁ ነዉ፡፡

ስለ ኢትዮጵያ ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ከምትጠይቀኝ ስለ ቸልሲ ተጫዋቾች የምግብ ምርጫ ብጠይቀኝ መልሱ አይከብደኝም፡፡ አንድም ቀን እዛ የምታዉቀዉ የአዲስ አበባ ስታዲየም ገብቸ የሀገሬን ክለቦች ጨዋታ አይቼ አላዉቅም፡፡ የቸልሲን ጨዋታ ለማየት ግን የልጄን የልደት በዓል አቋርጬ ወጥቻለሁ፡፡

Thursday, January 24, 2013

Meles Zenawi: The man who gave back

FIHESA ZENAWI, Sister of the Great Leader Meles Zenawi, talked to CCTV.

I said nothing but WOW,

What an interesting documentary by CCTV, watch via the link below. it is a 30 minute breathtaking documentary.


My sister took me to him and we took pictures and he was amazed that I had grown so old but I said I was fine. Later, when it was time to leave, my sister put some money in his children’s pockets. Marda and Senay were there. I was shocked, wondering what she was doing and thought to myself, “ he should be giving us money to buy some clothes; instead she is giving him money”. Later when we got home, I asked her why, since he had such an important job, she had to give him money and she replied to say “oh, my sister, there is one thing you don’t know. Meles doesn’t even know what a Birr note looks like…

Thursday, January 17, 2013

ትኩስ ድንች

ከረፋዱ 5፡00 ሠዓት ላይ ነዉ፡፡ ከመስሪያ ቤቴ ፈቃድ አግኝቼ ለግል ጉዳይ ከዘገየሁበት መርካቶ እየተመለስኩኝ፡፡ ከመርካቶ ወደ ፍልዉሃ በሚጓዘዉ ታክሲ ዉስጥ ተሳፍሬ የግል ጉዳዬን አወጣለሁ፤ አወርዳለሁ፡፡ ከኋላ ወንበር ላይ ተቀምጣ በስልክ የምታወራዉ ሴትዮ ድምፅ እየጎላ መጥቶ ወደ ሁላችንም ጆሮ መድረስ ጀመረ፡፡ ሴትዮዋ ከምታናግራት ሌላ ሴት ላይ በብስጭት ትደነፋለች፡፡ 

“እንዴት እንዲህ ትያለሽ? ተሳስተሻል እኮ፡፡” እያለች ትጮህባታለች፡፡ በዛኛዉ የስልኩ ጫፍ ያለችዉ /በኋላ እንደተረዳሁት የደወለቸዉ ሴትዮ የቢሮ ፀሀፊ ነች/ ነገሩን ቀለል ለማድረግ የሞከረች መሰለኝ የሴትየዋ ቁጣ እየከረረ መጣ፡፡

“አይባልማ፡፡ ነዉር እኮ ነዉ፡፡ በዚህ ሰዓት ሁሉም ሰራተኛ በስራዉ ላይ መገኘት እንዳለበት እያወቅሽ እየመጣች ነዉ ይባላል እንዴ?” ብላ በድጋሚ ተቆጣቻት፡፡ ወቀሳዋ አልበረደም፡፡ “ቆይ አሁን ሰራተኞችን ማነዉ የሚቆጣጠራቸዉ ይባላል? የኛን ሰራተኞች ደግሞ ታዉቂያቸዋለሽ፤ ሃላፊ ከሌለ ስራ አይሰሩ፡፡”

Saturday, January 12, 2013

መለስ ዜናዊ በአሌክስ ዲ ዋል ዕይታ

መለስ ዜናዊን ለምትወዱት ወይም ለምትጠሉት ብቻ፡፡ መሃል ሰፋሪዎች እንኳን ቢቀርባችሁም ግድ የለም፡፡ እናንተ መለስን የምትወዱ ወይም የምትጠሉ ግን እርሱን ስታደንቁም ሆነ ስትጠሉት አዉቃችሁት ቢሆን ያምርባችኋል፡፡ መለስን በደንብ አድርገዉ ከሚያዉቁት አለም አቀፍ ስብዕና ካላቸዉ ሰዎች አንዱ አሌክስ ዲ ዋል ነዉ፡፡ ይህ ብሪታኒያዊ መለስ ከበረሃ እስከ ቤተመንግስት ያለዉን ስብዕና በተከታዩ በጣም አጭር ፅሁፍ አብራርቶታል፡፡ 

ለነገሩ እርሱ ስለ መለስ የፃፈዉ ይህን ብቻ አይደለም ፡፡ ይችኛዋን ስታነቡ ግን አሌክስ ዲ ዋል ‘ከወደደ ወደደ፤ ከጠላ ጠላ’ የሚሉት አይነት ሰዉ እንዳልሆነ ትረዳላችሁ፡፡ ከአንድ ነገር ዉሰጥም ቢሆን የሚወደዉንና የሚጠላዉን ለይቶ የሚያዉቅ ነዉ፡፡ እሱ የወደደዉ ወይም የጠላዉ ሁሉ ግን ትክክል ነዉ እያልኩ አይደለሁም፡፡

አሌክስ ፀሃፊና ተመራማሪ ነዉ፡፡ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በሱዳንና ደቡብ ሱዳን ላይ ጥልቅ ምርምር ያካሄደ ምሁር ነዉ፡፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካም ከደርግ ግዜ ጀምሮ እስከ ሽግግሩ ወቅት ድረስ አብጠርጥሮ ያዉቀዋል፡፡ አሁን የወርልድ ፒስ ፋዉንዴሽን ዳይሬክተር ሲሆን የተለያዩ አለምአቀፍ ሃላፊነቶችም አሉት፡፡ አሜሪካ በሶማሊያ ዉስጥ አድርጋዉ የነበረዉን ወታደራዊ ጣልቃገብነትና አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሱዳኑ ፕሬዝዳንት ላይ የቆረጠዉን የእስር ማዘዣ አምርሮ የተቃወመ ነዉ፡፡ 

አሌክስ ይህን ፅሁፍ ከኢትዮጵያዊዉ አብዱል መሃመድ ጋር በመሆን ነዉ ያዘጋጀዉ፡፤ አብዱል ሞሃመድ በአፍሪካ ህብረት የሱዳን ጉዳይ ከፍተኛ የአስተግባሪዎች ፓነል ሃላፊ ነዉ፡፡ የነዚህን ሁለት ጎምቱ ምሁራንን ፅሁፍ ማንበብ መለስ ዜናዊን አዉቆ ለማድነቅ ወይም ለመቃወም ያግዛል ብዬ አሰብኩ፡፡ እነሆም ሼር አደረግሁላችሁ፡፡   

ምርጫ 2005

በመጪዉ ሚያዚያ የሚካሄደዉ የአካባቢ ም/ቤቶችና የአዲስ አበባና ድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤቶች ምርጫ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣዉ የግዜ ሰሌዳ መሰረት እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ ለምርጫ ሂደቱ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችና የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ከተጠናቀቀ በኋላ የዕጩዎችና መራጮች ምዝገባ በመካሔድ ላይ ነዉ፡፡ 29 የፖለቲካ ፓርቲዎችም የመወዳደሪያ ምልክታቸዉን ወስደዋል፡፡ 


የዚህ ፅሁፌ ትኩረት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምርጫዉ የሰጡት የትኩረት መጠን ይሆናል፡፡ “ለምን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ብቻ?” ብላችሁ እንደማትጠይቁኝ አዉቃለሁ፡፡ ምክንያቱም ኢሕአዴግ ልክ እንደ 2002ቱ ሀገራዊ ምርጫ ዘንድሮም ተቀናቃኞቹን በዝረራ ለማሸነፍ እየተጣደፈ መሆኑን እናዉቃለንና፡፡ ጥያቄዉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በ1997ቱ ሀገራዊ ምርጫ ኢሕአዴግን አዲስ አበባ ላይ የመዘረራቸዉን ታሪክ በዚህ አመትም ለመድገም የሚያስችላቸዉን ትኩረትና ዝግጅት አድርገዋል ወይ? የሚለዉ ነዉ፡፡ እንደኔ ለምርጫዉ የሰጡት ትኩረትም ሆነ ዝግጅታቸዉ ምርጫዉን የሚመጥን አይደለም፡፡


አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ገና ከጅምሩ ሲቋቋም የደጋፊዎቹንና የአባላቶቹን አላማ በማንገብ፤ በጥቅሉም የማህበራዊ መሰረቱን ጥቅም በማቀንቀን በሰላማዊ የፖለቲካ ዉድድር ላይ ተሳትፎ ገዢ ፓርቲ ለመሆንና የራሱን አላማ በመንግስት ስልጣን ለማስፈፀም ነዉ፡፡ ስለሆነም በምርጫዎች ሁሉ መወዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች ተፈጥሯዊ ባህሪ ነዉ፡፡