Monday, November 12, 2012

ግብረሰዶም በኢትዮጵያ፤ የመንግስትና የመገናኛ ብዙሃን ሚና

                                       
ኋላ ላይ ስሙን ከምነግራችሁ ወጣት ጋር አንዲት ጠባብ ክፍል ዉስጥ ቁጭ ብለን ቀስ በቀስ ህይወቱን አስቦት እንኳን ወደማያውቀ አዘቅት ስለከተተ የታሪኩ ክፋይ እያወጋኝ ፡፡ ከገጠመኙ እንጀምር፡፡ እናንተንና አምቡላንስምን እንደሚያመሳስላችሁ ቃላችሁ? አለኝ ካፌ ዉስጥ አጠገቤ ቁጭ ያለ የታክሲ ሹፌር፡፡ ኧረ አላቅም ስል መለስኩለት፡፡ ነቱን ለመናገር እንኳን መልሱን ጥያቄንም አልተረዳሁትም ነበር፡፡ ሹፌሩ ወደ ጆሮዬ ጠጋ አለና  እናንተም ልክ እንደ አንቡላንስ ከኋላችሁ ጭነት ታስገቡና ኡኡታችሁን ትለቃላችሁ ብሎኝ ወጣ፡፡ እኔ ግን ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ፡፡ በዙሪያዬ ያለ ሁሉ የሰማ ስለመሰለኝ ዞር ብዬ ለማየት እንኳን አልደፈርኩም፡፡  አለኝ ወጣቱ፡፡

የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች የጋራ ምክር ቤት የአመራር አካላት በጋራ የሚሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ እንድዘግብ የምሰራበት ተቋም /ኢሬቴድ/ መድቦኛል፡፡ አሁን በሂወት የሌሉትን አቡነ ሎስንና አሁን በስልጣን የሌሉትን ሼህ አህመዲንን ጨምሮ በርካታ የሃይማኖት አባቶች በአንድ ትልቅ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ይመክራሉ፡፡ ጋዜጠኞችንንም ቀጥረናል፡፡ እኛም ታዲያ መረጃ በተጠማ የህዝባችን ጆሮ ዉስጥ አንድ ነገር ልንሰነቅር ጓጉተናል፡፡ ጉዳዩ ደግሞ 16ኛዉ አለም አቀፍ የኤድስና ተላላፊ በሽታወች የአፍሪካ ኮንፈረንስ ቀደም ብሎ ሊካሄድ የታሰበ የግብረሰዶማዉያን ጉባዔ አጥብቆ የማገዝ ስለሆነ መረጃዉን ለማግኘት ቋምጠናል ብል ይቀለኛል፡፡ እኔም ዘገባዬን የተሟላ ለማድረግ ቢረዳኝ ብዬ ወደ አንድ በግብረሰዶም ለተጠቁ ሰዎች ድጋፍ የሚያደርግ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጎራ አልኩ፡፡ እዛ ታዲያ ገጠመኙን ከላይ ጋት ከጀመረልኝ ዳንኤል ጋር የተገናኘን፡፡

ዳንኤል ደጉ /ስሙ ለዚህ ፅሁፍ ሲባል ተቀይሯል/ ግብረሰዶም /ጌይ/ የሆነዉ 2001 ጀምሮ ፡፡ 21 አመቱ ዳንኤል የተወለደ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 280 .. ርቃ በምትገኘ ጨኮ በተባለች የገጠር መንደር ፡፡ 16 አመቱ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ ላቡን አንጠፍጥፎ በሚያገኘ ገቢ ቤተሰቦቹን የመደገፍ ራዕይ ሰንቆ ነበር፡፡ ለዳንኤል ፍላጎቴን ካስረዳሁት በኋላ ትክክለኛ ስሙን እንዳልጠቀም ቃል አስገብቶኝ ታሪኩን በዝርዝር አወጋኝ፡፡ ለነገሩ የሃይማኖት መሪዎቹ ይይት እንዳይዘገብ ስለተወሰነ መረጃዉን ያኔ አልተጠቀምኩበትም ነበር፡፡

ዳንኤል ጌይ የሆነ የታክሲ ረዳት ሳለ ፡፡ አንድ ቀን እንደተለመደ ከፒያሳ ወደ መገናኛ ባለ መስመር እየሰራ ሳለ አንድ አፍሪካዊ ተሳፋሪ 180 ሳንቲም መንገድ 10 ብርና አድራሻ የተፃፈበት ካርድ ትቶለት ይወርዳል፡፡ ለምን ይህን ያህል ቸር እንደሆነለት ያልገባዉ ዳንኤል ታዲያ ማታ ላይ በአድራሻ ይደልለታል፡፡ "ሶስት ደቂቃ ያህል አወራን፤ እኔ ግን የተረዳሁት ሒልተን ሆቴል 332 ቁጥር የእንግዳ ማረፊያ እንደሚገኝ ብቻ ው" ይላል ዳንኤል፡፡

የክፍሉን በር አንኳኳሁ፡፡ ከወገቡ በታች ፎጣ ብቻ ያገለደመ ጥቁር አፍሪካዊ በሩን ከፍቶ እንድገባ ጋበዘኝ፡፡ በሂወቴ እንዲህ የሚያምር መኝታ ቤት፤ የተለያዩ አይነት ቸኮሌቶች፤ መጠጦችና የመዋቢያ ቁሳቁሶች አይቼ አላቅም፡፡ ከሰ ጋር ጥቂት ቃላቶችን ከመለዋወጣችን በቀር ለራት እስከምንወጣ ድረስ ሌላ አላወራንም፡፡ ይኸ ደግሞ ለምን እንደፈለገኝ የማወቅ ጉጉቴን ጨመረ፡፡ ራት ከበላን በኋላ ከመዋኛ ገንዳዉ አጠገብ ወዳለ መናፈሻ ወስዶኝ ከዛ በፊት ቀምሼ የማላዉቀ የመጠጥ አይነት መጠጣት ጀመርን፡፡  ሂወቱን ለቀዉስ የዳረገዉን ያን እለት ሲተርክ ዳንኤል ፊት ላይ ጥልቅ ሀዘን ይነበባል፡፡

ከሳምንት በፊት ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ከደቡብ አፍሪካ እንደመጣ ነገረኝ፡፡ ብዙ ግዜ እኔ አድማጭ በሆንኩበት ወሬያችን መሃል ዬዉ እጄን መነካካት ጀምሮ ነበር፡፡ ለምን እንደፈለገኝ የተገለፀልኝ ግን ጉንጬን በተደጋጋሚ ሲስመኝና የጣቶቼን ጫፍ መምጠጥ ሲጀምር ፡፡ ከአቅሜ በላይ እየጠጣሁ ስለነበርና ደስ የሚል ስሜት ዉስጥ ስለገባሁ አልተቃወምኩትም፡፡ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ መቀመጫዬ ላይ የህመም ስሜት ነበረኝ፡፡ ማታ አንድ ግዜ የሚያሳምም 'ወሲብ' እንደፈፀምን አስታሳለሁ፡፡ ስቃዩ ግን አስር እጥፍ የሆነብኝ፡፡ ቅባት ነገር ሰጥቶኝ ራሴን እንዳስታምም ነገረኝ፡፡

ድምፁ መቆራረጥ ጀምሯል፡፡ ሆኖም ዳንኤል ታሪኩን መናገሩን አላቆመም፡፡ ኢትዮጵያን 15 ቀኖች ከሰሜን እስከ ደቡብ ጫፍ እየዞርን ስንጎበኝ እንልና ለሊቱን አብረን እናድራለን፡፡ ያልኩትን ሁሉ ይገዛልኝ ነበር፡፡ ያኔ ጀምሬም ታክሲ ላይ መስራቴን ኩ፡፡ አዲስ አበባ ስንመለስ ከሃገሩ ከመጡ የሱ ብጤዎች ጋር አስተዋወቀኝ፡፡ አብረን እንቅማለን፤ እናጨሳለን፤ ከሀገራቸ ያመጡትን ዕፅና አልኮልም አቅላችንን እስክንስት እንወስዳለን፤ ከዛም 'ወሲብ' እንፈፅማለን፡፡ እንባ የተሞሉ አይኖቹን እንዳላይበት አቀርቅሮ ነበር የሚያወራኝ፡፡

ዳንኤል አሁን የኤች አይ ቫይረስ በደሙ ዉስጥ ይገኛል፡፡ የጤና መታወክም በየግዜ ያጋጥመዋል፡፡ በመሆኑም ቤተሰቡን የመደገፍ ቀርቶ የእለት ጉርሱን እንኳን ሰርቶ ማግኘት አልቻለም፡፡ ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ ሆኖ አሁን መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ትንሽም ቢሆን ይደግፈዋል፡፡ የፀረ-ኤች አይ መድሃኒትም እየወሰደ ይገኛል፡፡

ታሪክ የመጀመሪያዎቹ የግብረሰዶም ጥንዶች አድርጎ የመዘገባቸ ኩንሆቴን እና ኒያንክኑሀም የተባሉ ግብፃያን ወንዶች ናቸዉ /2400A.C/፡፡ በጥንታዊ ሮምም ይህ ነገር አዲስ አይደለም፡፡ ያኔ ታዲያ በባሪያ ንግድ የተገበዩ ጥቁር ወንዶች የሴቷን ሚና ሲይዙ ጌቶቻቸዉ የወንድነት ድርሻቸ ይወጡ ነበር፡፡ ፍሎረንስና ቬኑስን የመሳሰሉ ያኔ የደመቁ የጣሊያን ከተሞችም በግብረሰዶም መስፋፋት የታወቁ ነበሩ፡፡

ምንም እንኳን ብዙ ወንድ ጥንዶች በዚህ ያልተገባ ተግባር ስጥ ቢገቡም  የየሀገራቱ ባለስልጣናት ግን ግብረሰዶምን በወንጀልነት ፈርጀዉ ፈፃሚዎችን በህግ ይቀጡ ነበር፡፡ 13ኛዉ /ዘመን አጋማሽ ጀምሮ በብዙዎቹ የአዉሮፓ ሀገራት እስከሞት የሚያደርስ ቅጣት ያስፈርዳል፡፡ 

አሁን በአለም ላይ ያለ የግብረሰዶማዉያን ቁጥር በርግጠኝነት ለመናገር የሚያስችል መረጃ የለም፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በዘመነዉ የምዕራቡ አለም 1-3 በመቶ ያክሉ ዜጎች ግብረሰዶማዉያን ሲሆኑ 2-10 በመቶ ያክሉ ደግሞ ቢያንስ አንድ ግዜ ከተመሳሳይ ፆታ ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ፈፅመዋል፡፡ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ብቻ 5 ያክል ወንድ ግብረሰዶማዉያን እንዳሉ ይገመታል፡፡ ይህ ቁጥር አስደንጋጭ ቢሆንም ከጉዳዩ ድብቅ ባህሪ አንፃር የቁጥሩን ነታነት ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ነዉ፡፡

በአለም አቀፍ ሆቴሎች ዙሪያ ያሉ የአዲስ አበባ መንገዶች ሀገር ዜጎች የሚያዘወትሯቸ የምሽት ክለቦችና ደላሎች በርካታ ኢትዮጵያያን ወጣቶች የዉጭ ሀገር ዜጎችን ፍላጎት ለማርካት እኩይ ተግባር የሚመለመሉባቸ ስፍራዎች ናቸ፡፡ በተጨማሪም የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች የሚያሳዩት አስገድዶ መድፈር የሚፈፀምባቸ ህፃናትና ወጣት ወንዶች  ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ፡፡ የዚህ አይነት ወንጀሎች በአመት እስከ 300 ያክል ይፈፀማሉ፡፡ ከነዚህ ስጥ ጥቂቶቹ ብቻ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚመጡና እነሱም ቢሆኑ ዝቅተኛ የቅጣት ሳኔ እንደሚተላለፍባቸ መረጃዎች የሚያመለክቱት፡፡

ሰይፉ ሐጎስ በዘርፉ ያደረጉት ጥናት በኢትዮጵያ የጤና ማህበር /EPHA/ መፅሄት ላይ ታትሞላቸዋል፡፡ እርሳቸ እንደሚሉት ግብረሰዶም አሁን ለኛ ማህበረሰብ እንግዳ ነገር መሆኑ አብቅቶለታል፡፡ አብሮን ያለ ልማድ ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ እንደሳቸዉ ጥናት ግብረሰዶም እንዲባባስ ያደረጉት የዉጭ ሀገር ዜጎች ናቸ፡፡ የሃገራችን ታዳጊ ወጣቶች ለገንዘብ ሲሉ ወደዚህ ጎራ ይሰለፋሉና፡፡

የተደራጁ የግብረሰዶማዊያን ንቅናቄና የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞችን ኡኡታን ተከትሎ አሁን ግብረሰዶም ከዲሞክራሲ መብቶች ጥያቄ ጋር መያያዝ ጀምሯል፡፡ ቀድሞ ግብረሰዶምን አጥብቀ የተቃወሙና በህግም ጭምር ከለላ ያደረጉ ሀገሮች አሁን በአቋማቸዉ ላይ መለሳለስ እያሳዩ ፡፡ በፈረንጆቹ 2012 መጀመሪያ ላይ ኤቢሲ ኒዉስ በዋሽንግተን ያደረገ የህዝብ አስተያየት ዳሰሳ ግብረሰዶምን የሚደግፉ ሰዎች በትንሽ ቁጥርም ቢሆን ለመጀመሪያ ግዜ ከሚቃወሙት በልጠ ተገኝተዋል፡፡ 2006 የግብረሰዶማዊያን ጋብቻ ህጋዊ ሊሆን ይገባዋል ያሉ አሜሪካያን ድርሻ 36በመቶ ነበር፤ በዚህኛዉ ጥናት ግን 53በመቶ ደርሷል፡፡

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ባለፈዉ ግንቦት /2012/ የግብረሰዶማዉያንን ጋብቻ እንደሚደግፉ ግልፅ አድርገዋል፡፡ ተቺዎች ያኔ አሁን በድል ለቋጩት 2012 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድጋፍ ለማግኘት ያደረጉት ሲሉ ተችተዋቸዉ ነበር፡፡ እርሳቸ ተከትሎም የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የግብረሰዶማዉያንን መብት ለማያስከብሩ የአፍሪካ ሀገራት እርዳታ እንደማይለግስ ጠቁሟል፡፡ በዚህ ሳምንት /2013/ ደግሞ የፈረንሳይ መንግስት ካቢኔ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን የሚፈቅድ  ረቂቅ ህግ ጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ ምንም እንኳን የግብረሰዶም ደጋፊ ንቅናቄዎች ቢኖሩም ነባራዊ ሁኔታ ከዘመነ የምዕራቡ አለም በተለይም ከአሜሪካ እጅጉን የተለየ ፡፡ በዚህ ላይ ከሞላ ጎደል ያልተከፋፈለ ጥላቻና ተቃ በህዝቡ ዉስጥ ያለ፡፡ 2000 . የተለያዩ የሀይማኖት ተቋማትና የመንግስት ተወካዮች በአንድ ላይ ተሰባስበ እየተስፋፋ የመጣ የግብረሰዶም ተግባር ከሀይማኖትና ባህላችን የወጣ አፀያፊ ተግባር ሲሉ በአንድነት ግዘታል፡፡ መንግስት ጠንከር ያለ ቅጣት በአጥፊዎች ላይ እንዲወስድም ጠይቀዋል፡፡ በነዚህ ሰዎች የተያዘ አቋም የመላ ህብረተሰብ እምነት የሚወክል ፡፡

የኢፌድሪ ህገ-መንግስት ለሰብዓዊ መብቶች እዉቅና ይሰጣል፤ አለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችንም ይቀበላል፡፡ ሆኖም እነዚህ መብቶች የሕዝብን ሰላም፤ ጤናንና ሞራል መጠበቅ ላይ በተመሰረቱ ዝርዝር ህጎች ሊገደቡ እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡ ይህ በግልፅ የሚያሳየዉ መንግስት ከግለሰቦች መብት ባለፈ የማህበረሰቡን ባህል፤ ልማድና ሃይማኖት የመጠበቅና የማገልገል ህገ መንግስታዊ ሃላፊነት  እንዳለበት ፡፡

በተመሳሳይ ፆታ መካከል 'ወሲብ' መፈፀም በበርካታ ሙስሊም ሀገሮች በሞት ያስቀጣል፡፡ አረቢያ፤ ኢራን፤ ሰሜን ናይጀሪያ፤ ሱዳንና የመንን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአፍሪካ፤ በመካከለኛ ምስራቅና በኤስያ በርካታ ሀገሮች ግብረሰዶም በህግ የሚያስቀጣ ከባድ ወንጀል ነዉ፡፡ በአንፃሩ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም በአንድ ድምፅ ግብረሰዶምን በሚያወግዝባት ኢትዮጵያ ግን በግብረሰዶማዉያን ላይ የሚጣለዉ 3-4 አመት የእስር ቅጣት ብቻ ነዉ፡፡ ይህም ከስንት አንዴ ነዉ የሚተገበረ፡፡

በአንድ ወቅት እንደሰማሁት /ቀልድ ይሁን ቁምነገር ያላረጋገጥኩት ወሬ/ የግብረሰዶም አቀንቃኞች ናቸ አሉ፤ ታላቁን መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን መስቀል አደባባይ ወጥተን ድምፃችንን ማሰማት እንፈልጋለን፤ ይፈቀድልን ሲሉ ይጠይቋቸዋል፡፡ ብልሁ መሪ ታዲያ ትችላላችሁ ግን የደህንነት ከለላ ልንሰጣችሁ አንችልም ይሏቸዋል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍን ፈቅዶ የስርዓት አስከባሪዎችን ጥበቃ መንፈግ ሰልፉን ከመከልከል አይተናነስም፡፡ የጠ// ምላሽ ስጠ ወይራ የሆነባቸዉ ጌዮቹ ታዲያ አመስግነዉ ከቤተመንግስት ወጡ፡፡ ቢያንስ በዚች ሀገር ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት እንዳላቸ ተረድተዋልና፡፡ አንዳንዶች ታዲያ // መለስ ይህንን የፈቀዱት ህዝቡ ብሎ በመዉጣት በድንጋይ እንደሚወግራቸ ስላመኑ ሲሉ ግምታቸ ሰጥተዋል፡፡ 

በመንግስት በጀት የሚተዳደሩ የመገናኛ ብዙሃን ስለግብረሰዶም ምንም አይነት ዘገባ እንዳያሰራጩ የኤዲቶሪያል ፖሊሲያቸ ያዛቸዋል፡፡ በመሆኑም ግብረሰዶምን የሚደግፍም ሆነ የሚቃወም ዜናም ሆነ ሀተታ አንሰማም፤ አናይም፡፡ ችግሩ ባልተፈታበት ይልቁንም በሁለቱም በኩል ትግሉ በቀጠለበት ሁኔታ መንግስትና መገናኛ ብዙሃኖቹ የተከተሉት የዝምታ ፖሊሲ /Dont ask, dont tell policy/ እስከ መቼ ያዘልቅ ይሆን?

Post a Comment