Monday, October 15, 2012

እውቅና እና እውቀት፤ ዱባ እና ቅል


ለዛሬው ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ በዚሁ ሳምንት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሴቶች ፕሮግራም የተላለፈ ሴቶች በማስታወቂያ ላይ የሚጫወቱትን ሚና የተመለከተ ዘገባ ነ፡፡ ከሁሉ በፊት አዘጋጇን ጋዜጠኛ ላደንቃት እፈልጋለሁ፡፡ አዘጋጇ የብዙዎች መነጋገሪያ የሆነን ርዕሰ ጉዳይ መርጣ የሚመለከታቸን ባለድርሻዎች በሙሉ በማነጋገር እንዲከራከሩበት አድርጋለች፡፡

ከይዘቱ በዘለለ የእኔን ትኩረት የሳበ ግን በእቅናና በእቀት መካከል ያለ ልዩነት ነ፡፡ በኔ እምነት በዚህ ዘገባ እቅና ያላቸዉ እቀት ሲያጥራቸ በአንፃሩ እኛ የማናቃቸ አዋቂነት ታይቷል፡፡

በቴሌቪዥን በሚታዩ ማስታወቂያዎች የሴቶች አተዋወን ቢያንስ ሶስት ችግሮች እንዳሉበት ተመልካቾች በዘገባ ላይ አንስተዋል፡፡ በአንዳንድ ማስታወቂያዎች ላይ በሚተዋወቀ ምርት/አገልግሎትና በሴቷ አስተዋዋቂ መካከል ምንም አይነት ምክንያታዊ ትስስር አናይም፡፡ “አዲስ የመኪና ሞዴል የምታስተዋዉቅ ተዋናይ መኪናዋን እየዞረች ስትነካካ እናያለን፡፡” የማስታወቂያ ባለሙያ ግን በአስተዋዋቂዋና በተስተዋዋቂዉ ምርት መካከል ያለን ግንኙነት አያሳየንም ሲሉ አብነት ያነሳሉ፡፡ ተዋናይቷ መኪና ማሽከርከር ስለመቻሏ እንኳን ማስረጃ አናገኝበትም ሲሉ ተችተዋል፡፡ ስለሆነም ማስታወቂያ ሲያልቅ ከኛ አዕምሮ የሚቀረዉ አንድም የመኪናዋ አለዛም የልጅቷ ምስል ብቻ እንጅ አዲሷ መኪና ይዛ የመጣችዉ የጥራት ደረጃ አይሆንም ነ የሚሉት፡፡

ሌላዉ የማስታወቂያዎች ችግር የሴቶች የአወካከል ገፅታ ነዉ፡፡ ሴቶች በብዙ ማስታወቂያዎች የሚወከሉት በተለምዶ “የሴቶች” ተብለ በተፈረጁ የስራ መስኮችና “ዝቅተኛ” በሚባሉ የስራ አይነቶች ነ፡፡ አንዱ ተመልካች “ካፌና ምግብ ቤት ጎራ ስንል ወንዶች በብቃት ሲያስተናግዱ እናያለን፤ ሆኖም በመስተንግዶና ምግብ ዝግጅት ትምህርት ቤቶች ማስታወቂዎች ላይ የምናያቸ ሴቶችን ብቻ ነ፡፡" ሲል አግራሞቱን ገልጧል፡፡ 

ሌላደግሞ ሴቶች ሁልግዜ የስራ አስኪያጅ ፀሃፊ እንጅ ስራ አስኪያጅ ሆነ አናያቸም ሲል ቅሬታን አቅርቧል፡፡ ሳሙና ከተዋወቀም ሁሌ አጣቢዎቹ ሴቶች ናቸ ብሏል፡፡ እናም ማስታወቂያዎቻችን አሁን እየቀነሰ ቢሆንም ላልተወገደ የተዛባ ስርዓተ ፆታ ጠበቃ ሆነዋል ነ ትችቱ፡፡

የሴቶችን ገላ ለምርት/አገልግሎት ማሻሻጫ መጠቀምም የማስታወቂያዎቻችን ችግር ሆኖ ቀርቧል፡፡ በአስተዋዋቂዋ አማላይ ዉበት ተማርከን ምርቱን/አገልግሎቱን እንድንገዛ የሚፈልጉ ነገር ግን ስለሸቀጡ የማይነግሩን አሉ ነ ያለው ሌላው አስተያየት ሰጭ፡፡ እነዚህ ቅሬታ ያዘሉ አስተያየቶች የተሰነዘሩባቸው የማስታወቂያ ባለሙያወችና አስተዋዋቂዎች ታዲያ የየራሳቸን ምላሽ ይዘው ቀርበዋል፡፡ እኔን የሳቡኝና ቅሬታዬን እንዳቀርብ የገፋፉኝ ታዲያ የተሰጡት መልሶች ናቸ፡፡

አንድ በሃገራችን የኪነ-ጥበብ ኢንዱስትሪ ስማቸው የገነነ፤ የማስታወቂያ ድርጅት ባለቤትና ታዋቂ የማስታወቂያ ሰራተኛ /ልብ በሉ ታዋቂ እንጅ አዋቂ አላልኩም/ በሰጡት ምላሽ ወንድ ፀሃፊ ‘ሃሎ’ ከሚለኝ ሴት ፀሃፊ ‘ሃሎ’ ብትለኝ ደስ ይለኛል፡፡” አሉ፡፡ እኝህ ባለሙያ የርሳቸውን እውነታ የሁሉም ዜጋ እውነታ /general truth/ አድርገው ሲያቀርቡም ይታያሉ፡፡ “ይኽ እኮ የታወቀ ነ፤ ሴቶች ፀሃፊ፤ ነርስና የበረራ አስተናጋጅ መሆን ቦታቸው ነው፤ ተፈጥሯቸው ነው፡፡ ወንድ ደግሞ ከባድ መኪና ለማገላበጥ፤ የጉልበት ስራ ለመስራት፤ ለጋራዥ ስራ ይመረጣል፡፡”  ሲሉ ቃል በቃል የአመለካከታቸዉን ምጥቀት አሳይተውናል፡፡

ዛሬም በ21ኛዉ ክ/ዘመን ላይ ሆነን ‘የሴቶች’ እና ‘የወንዶች’ ብለን የፈረጅናቸው የስራ አይነቶች መኖራቸው ትዝብት ውስጥ የሚከተን ነው፡፡ እኝህ ታዋቂ ሰው ያላወቁት ወይም ያልተገለጠላቸው ግን እንደ ዶክተር እሌኒ ገ/መድኅን ያሉ ሴት ስራ አስኪያጆች፤ እንደ ዶክተር ሊያ ታደሰ ያሉ ሴት ስፔሻሊስት ዶክተሮች፤ እንደ ካፕቴን አምሳለ ጓለ ያሉ ሴት የአዉሮፕላን አብራሪዎች …ወዘተ የመኖራቸው እነታ ነ፡፡

 እኝህ ባለሙያ የሚገራርሙ የስራ ገጠመኞች አሏቸ፡፡ አንዱን ልድገምላችሁ፡፡ ከ6 ወይም 7 አመት በፊት ነ አሉ፤ የገላ ሳሙና ለማስተዋወቅ አንዲት ቆንጆ ልጅ ፓንት ብቻ እንድትለብስና ባኞ ቤት እንድትጠቀም አደረግን አሉ፡፡ ታዲያ “ህጉ እርቃን መሆንን ስለሚከለክል በ ‘መከራ’ አስፈቅደን ነ የሰራነ ሲሉም ጠቆሙን፡፡ ህጉ ይህን ከከለከለ የተፈቀደበት የ ‘መከራ’ አይነት ምን እንደሆነ የሚያቁት እንግዲህ እሳቸ፤ ፈቃጁና ሁሉን የሚያ ፈጣሪ ብቻ ናቸ፡፡ 

ዞሮ ዞሮ ከዛ ሁሉ 'መከራ' በኋላ “ቆንጆ ማስታወቂያ ተሰራ” አሉ ባለሙያ፡፡ ታዲያ ትንሽ እንኳን ፈቀቅ ሳይሉ አንዱ ስልክ ደወለልኝና ያች ልጅ ጭኗ እንዴት ደስ ይላል እባክህ አለኝ፤ ሳሙናን አላየም ማለት ነ ሲሉ ያንን ቆንጆ ያሉትን ማስታወቂያ አፈር አበሉት፡፡

ሌላ የፊልምና የማስታወቂያ ታዋቂ ባለሙያ ደግሞ ምላሽ አሰጣጣቸ ሲታይ “እርስዎ የሚሰሯቸ ማስታወቂያዎች ምን ያህል አስተማሪ ናቸዉ?” ተብለ በጋዜጠኛዋ የተጠየቁ ይመስላሉ፡፡ ለኝህ ታዋቂ አርቲስት በ30 ሰከንድ አስተማሪ የሆነ ማስታወቂያ መስራት የቋጥኝ ያክል ከብዷቸዋል፡፡ እርሳቸ “አስነጋሪ የሚመጣ ለመሸጥ ነ፡፡ ለማስተማር አይደለም፡፡ ይህ የመገናኛ ብዙሃን ስራ ነ፡፡ ለ30 ሰከንድ በምትታይ ድ የአየር ሰዓት ላይ አስተምሩ ከምትሉን እናንተ ስሩት” ሲሉ ጋዜጠኛዋን በነገር ሸንቆጥ አደረጓት፡፡ “እኛ ይህን የምንሰራ/የምናስተምረ/ በፊልማችን ነ፡፡” ሲሉም በራስ መተማመን መንፈስ ተናገሩ፡፡ 

ታዲያ እኔም ስራ አልፈታሁ፡፡ ፊልም ላይ እስከዚህም ነኝና ወደ አንድ ፊልም ወዳጅ ጓደኛዬ ጠጋ ብዬ በሰማያዊ ፈረስ ፊልም ላይ የተዋናያን አሳሳል ምን ይመስላል ብየ ጠየቅሁት፡፡ እሱ እንደነገረኝ ግን ወንዱ ዋና ተዋናይ/protagonist character/ የመጠቀ ሳይንቲስት ሚና ሲኖረዉ ሴቷ /antagonist character/ ግን የኋላ ታሪኳ በወንጀል የታጀበ ሰላይ ሆና ነ የምትተ፡፡

አንድ አስተያየት ሰጭ በርግጥ ባለሙያዎቻችን በማስታወቂያዎች እንዲያስተምሩ ህግ አያስገድዳቸም ሲል አዲስ ሙግት ጀመረ፡፡ ሆኖም “የሚሰራ ማስታወቂያ ህዝቡ ላይ ሊፈጥረ የሚችለን ተፅዕኖ በጎ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸ፡፡ ይህ ደግሞ በሁሉም ሙያ ስጥ አለ” ሲል ሌላ ወጣት የማስታወቂያ ባለሙያም “ከጥቅማችን ባለፈ ማህበራዊ ሃላፊነት አለብን፡፡” በማለት ሀሳቡን ደግፎታል፡፡

በርግጥ በነዚህ ታዋቂ ሰዎቻችን መልስ ተከፍቻለሁ፡፡ እቅና ባልተጎናፀፉት ጀማሪ የማስታወቂያ ባለሙያዎቻችን ግን ኮርቸባቸዋለሁ፡፡ ቢያንስ ጥሩን ከመጥፎ መለየት ችለዋልና፡፡ አንዲት ወጣት የማስታወቂያ ሰራተኛ አሁን ያለ ሁኔታ ጥሩ እንዳልሆነ መገንዘቧን ከዘገባ እንረዳለን፡፡ ግን “ገንዘብና ዝና ስለምንፈልግ እንቢ የማለት/ካላመነችበት/ ደረጃ ላይ አልደረስንም … እኔ እንቢ ብለ ሌላዋ ቆንጆ ጋር ሄዶ ያሰራል” ስትል ብሶቷንም ብስለቷንም ገልፃለች፡፡ ታዲያ ይች ወጣት ደግማ ትመጣና ለገንዘብና ዝና ስንል የጎደፈ፤ የማህበረሰብ ሞራልና አስተሳሰብ የሚጎዳ ነገር መስራት የለብንም” በማለት ራሷንና ሌሎችንም ቆንጆዎች መክራለች፡፡ ሌላ ገና ብዙም ያልታወቀ የማስታወቂያ ባለሙያና ሰራተኛም “ይህን የምናደርገ እሷን /ሴቷን አስተዋዋቂ/ ለማየት ሲል እቃዉን ያየዋል እያልን ነ፡፡ ይሄ ሙሉ በሙሉ መቀረፍ ያለበት ነ፡፡” በማለት የሷን ሃሳብ አጠናክሮታል፡፡

ይህ ጉዳይ ግን ከማስታወቂያ አዘጋጆችና አስተዋዋቂዎች ባለፈ የመገናኛ ብዙሃንንም ትኩረት የሚሻ ነ፡፡ አብዛኞቹ የምስል ማስታወቂያዎች /commercial ads/ ለተመልካች እየደረሱ ያሉት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አማካኝነት ነ፡፡ እነት ነ የተቋሙ ተወካይ ተገቢ ያልሆኑ ማስታወቂያዎች እንዳይተላለፉ የሚያግዱ ህጎችን በዘገባ ላይ ዘርዝረዋል፡፡ ኢ.ሬ.ቴ.ድ. የማስታወቂያ ፖሊሲ እንዳለም ነግረዉናል፡፡ ይሁንና እነዚያ ቅሬታ የቀረበባቸማስታወቂያዎች የተቋሙን የይለፍ ፈቃድ ሲያገኙ ፖሊሲ ጥርስ የሌለዉ አንበሳ እንደነበር አላረጋገጡልንም፡፡ በተለይ ደግሞ ታዋቂ የማስታወቂያ ድርጅት ባለቤት በህግ የማይፈቀድ ያሉትን ማስታወቂ በ መከራ’ ሲያሳልፉ ህግ መጣሱን ሊነግሩን ይገባ ነበር፡፡

እኔ ሴቶችን ለማስታወቂያነት መጠቀም ተገቢ አይደለም የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሴትነት በማስታወቂያ ላይ ልዩነት አይፈጥርም ብዬም አላምንም፡፡ አለም በ1860ዎቹ በጀምስ ዱክ የሲጋራ ማስታወቂያዎች የጀመረና እስካሁን የገፋበት የሴቶች አስተዋዋቂነት ሚና በንግዱ ዘርፍ ጉልህ ሚና ተጫዉቷል፡፡ ፈረንጆች sex sells ይሉታል ጤታማነቱን ለመግለፅ፡፡

ከዚሁ ጋር የተያያዘዉ ሌላ ችግር በአብዛኛዎቹ የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች “ምርጥ” አስተዋዋቂ ተብለ የሚቀርቡት በጣም ቀጫጭንና ወጣት ሴቶች ከመሆናቸ ጋር በተያያዘ የተከሰቱት አሉታዊ አንደምታዎች ናቸ፡፡ የእነዚህ ‘ሸበላዎች’ የቴሌቪዥን እይታ ተፈጥሯዊ ገፅታቸን እንደማይወክል ስጠ አዋቂዎች ይሞግታሉ፡፡ የካሜራና ኤዲቲንግ ባለሙያዎች ሴቶቹን ‘ፍፁማዊ በት’ /image of perfection/ ለማላበስ ሳይንሱን ይጠበቡበታል፡፡ ያም ሆኖ ከጭ ያሉ ወጣት ሴቶች አስተዋዋቂዎቹን መስሎ ለመገኘት አዕምሮአቸንና ሰነታቸን ያስጨንቃሉ፤ ገንዘብና ግዜያቸን ያፈሳሉ፡፡ ይህን ማድረግ ያልቻሉት ደግሞ የበታችነት ስሜት /inferiority complex/ ተሸካሚ ይሆናሉ፡፡

ዘ ቢዩቲ ሚዝ የተሰኘ መፅሃፍ ደራሲ ናኦሚ ወልፍ “እኛ ሴቶች አሁን የበዛ ገንዘብ፤ ከፍ ያለ ተሰሚነትና የተሻለ የህግ እውቅና አለን፡፡ በራሳችን ተክለ ሰነት ላይ ያለን ነፃነት ግን በጭቆና ስር ከነበሩት ሴት አያቶቻችን ያነሰ ነ፡፡” ብላለች፡፡ ለዚህም መገናኛ ብዙሃንንና የማስታወቂያ ኩባንያዎችን ኮንናለች፡፡

የዚህ ምስለ እንስቶች ተፅዕኖ ግን በሴቶች ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ወጣት ወንዶችም የሴቶች በት መለኪያ ሚዛኑ በቴሌቪዝን የሚታየዉ ‘ፍፁማዊ በት’ እንደሆነ አድርገ እየወሰዱት ነ፡፡ እንደ ቶም ሪቸርት አነጋገር /የ ዘ ኢሮቲክ ሂስትሪ ኦፍ አድቨርታይዚንግ ደራሲ/ የማስታወቂያ ኢንዱስትሪ ከምግብ ፍላጎት ማጣትና /ክብደት ለመቀነስ/ ዘመናዊ የጡት ተከላ ህክምና በፍጥነት እየጨመረ መሄድ ጀምሮ እስከ የበታችነት ስሜት መፍጠር ድረስ ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀሶች ፈጣሪ ተደርጎ መወሰዱ ተገቢ ነዉ፡፡

አሁን ጥያቄ የሴት ልጅ ክብር ወይስ ገንዘብ የሚለ፡፡ እኔ ሀገራዊና አለማዊ ሁኔታዎችን እንዲሁም ባህላችንን ግምት ስጥ በማስገባት ሁለቱንም አጣጥሞ መሄድ ይቻላል ብዬ አምናለሁ፡፡ ግን ማስታወቂያ አዘጋጆቻችን የተዛባ የስርዓተ ፆታ አመለካከትን ቢያንስ ያለመሸከምና ግባቸን በሚያሻሽጡት ምርት/አገልግሎት ላይ እንጅ በአስተዋዋቂዋ ላይ ማድረግ እንደሌለባቸ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

Post a Comment