Thursday, September 13, 2012

“ጭንጋፍ የህዝብ ርኩስ- የሬሳ ጀግና”


ዉድ አንባቢዎቼ፤ አያቴ “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባ” ትል ነበር፡፡ እዉነትም የዘንድሮዉ መስከረም ጉድ ይዞ ነዉ የመጣዉ፡፡ ከጉድም ጉድ በህዝብ ላይ የመጣ ዉርጅብኝ፡፡ በርግጥ አንዳንዶቻችሁ /ይህን የማህበራዊ ድህረ ገፅ ሥራዬ ብላችሁ የያዛችሁቱን ማለቴ ነዉ/ ‘አልሰሜን ግባ በለዉ፤ ከዚህ በላይ ስንት ተብሎ የለ እንዴ’ እንደምትሉኝ እጠረጥራችኋለሁ፡፡ ሆኖም  እድሉን አግኝታችሁ የማታዩት ትበዛላችሁ ብየ ስላሰብኩ ይንን ጉዳችሁን እንድትሰሙት ሙሉ ግጥሙን ጭኘላችኋለሁ፡፡ 
ግጥሙን ያገኘሁት የሀበሻ ቲዩብ ዶት ኮም ላይ ነዉ፡፡ የፃፈና ያነበበዉ ደግሞ ሔኖክ የሺጥላ የተባለ /ካልተሳሳትኩ በአሜሪካ የሚኖር/ የኢሳት ቴሌቪዥን ቋሚ  ገጣሚ ነዉ፡፡ ወጣቱ የሀገራችን ፀሀፊ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማዉ ደስታ ከፍተኛ መሆኑን ግጥሙን ስታዳምጡ ትረዱታላችሁ፡፡ ሆኖም በዛዉ ልክ የሀገሩ ሰዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት የተሰማቸዉ መሪር ሀዘን ደስታዉን አስረስቶ “የኖርኩበት ሀገር የሌላ እስኪመስለኝ፤ አሁንስ አመመኝ” ሲል ትሰሙታላችሁ፡፡ 

ይኽ “ወዳጃችን” ምንም እንኳን በአካል እዚህ ባይኖርም ቀልቡ ሁሉ እዚሁ በመሆኑ ኢትዮጵያዉያን ሃዘናችዉን የገለፁበትን መንገድ ጠንቅቆ አዉቆታል፡፡ ይህን ካየ በኋላም እንደ ወዳጁ ኤልያስ ክፍሌ /የኢትዮጵያ ሪቪዉን አሳታሚ ማለቴ ነዉ/ “ኤዲያ የኢትዮጵያ ህዝብስ የሚታገልለትን አያዉቅም” ከሚል ማደማደሚያ ላይ የደረሰ ይመስላል፡፡ እናም የጀመረዉን “ትግል” በዚች ትንሽ ፈተና ተሸንፎ እንዳይተወዉ ስጋቴ ነዉ፡፡
እናንተ በጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ሞት ሀዘናችሁን በተለያየ መንገድ የገለፃችሁ የሀገሬ ልጆች፤ እመኑኝ ይህ የአብራካችሁ ክፋይ የምድራችሁ ብቃይ እንዲሁ ብሎ በነጩ ሰድቧችኋል፡፡ ካላመናችኁኝ ደግሞ ሙሉ ግሙን አዳምጡት/አስር ደቂቃ ብቻ ነዉ/፡፡ እናም አዳምጣችሁ ስትጨርሱ ከናንተዉ ጋር አፈር ፈጭቶ ያደገዉ ልጃችሁ እነዚህን ስድቦች ለመስከረም ገፀ-በረከተ እንደላከላችሁ ታረጋግጣላችሁ፡፡
እናንተ አልቃሾችና ሀዘንተኞች፤
·         ሚስትና ዉሽማ
·         ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ
·         ግብረ አመድ አፋሽ
·         መሰሪ
·         እዉነት የገደፉ…ዘንድሮም ያደፉ
·         አዛኝ ቅቤ አንጓች ትንሽ የማያፍሩ
·         ታሪክ ያባለጉ
·         የሬሳ ጀግና
·         እሾህ…አጋም
·         ህዝብ የሚባል መንጋ
·         ጭንጋፍ የህዝብ ርኩስ
·         አህያ…አልጋ ሲሉት አመድ
·         ፍናፍንት ጮሌ የማንነት ስቃይ
·         የባንዳ ከበሮ
·         የርጉም ዘመን ልጆች


Post a Comment